በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በደበረ ታቦር ከተማ አስተዳደር መኪና ያላቸው ተቋማት የተለያዩ የሞተር ዘይቶች እና ቅባቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ በተጠቀሰው የጨረታ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
- ያቀረቡት ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ማቴሪያሎችን ዝርዝር መግሰጫ (ሰፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃዎች ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም ደብር ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ኮፒ እና ኦርጅናል ሥርዝ ድልዝ በሌለበት የተጫራቾችን ሥም፣ ፊርማ፣ ማህተም፣ ጨረታው ያወጣው መ/ቤት ሥምና አድራሻ በመግለፅ በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ባሉት ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ግዥ ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡10 ይከፈታል፡፡
- በጋዜጣ የወጣው ጨረታ የሚከፈትበት ሰዓት በዓል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚታሸገውና የሚከፈተው በሚቀጥሰው የሥራ ቀን ሰዓቱን ጠብቆ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመሰለ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳንዱን ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መግለፅ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከነጠላም ዋጋ ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ በተጫራቾች ላይ የሚሞላ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ቢሆንም ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጨራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው (ተመስርተው) መጫረት አይችሉም፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ውድድሩ በሎት ስለሆነ አንደም እቃ ሳይሞላ መቀረብ የለበትም ሳያሞላ ከተገኘ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- የእቃው መጠን እስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- መምሪያው በጨረታ ሰነድ ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ የመረጠውን ዓይነት የመግዛት መብት አለው፡፡
- እቃው የሚቀርብበት ቦታ ደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ድረስ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ወይም በስልክ ቁጥር 058 441 02 09 /058 141 93 75 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ