በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በወረዳዉ ላሉ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚዉሉ የመኪና መለዋወጫ እቃ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠተሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከማዕ/አ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመክፈል ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነና ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ህዳር 30/2018 ዓ.ም 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ህዳር 30/2018 ቢሮ ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ታሽጎ 3፡05 ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቅዳሜና እሁድ ወይም በአል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እና በተመሳሳይ ለዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

