በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
75

የደጎሎ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ ማለትም ሎት 1 የቧንቧ መገጣጠሚያና ቧንቧ ቆጣሪ እቃዎችን በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ ማንኛውም ድርጅት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ማቅረብ ላይ የተቀመጡትን ዝርዝር ዋጋ በትክክል ማስቀመጥ አለባቸዉ፤ ሥርዝ ድልዝ ያለዉ በመ/ቤቱ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  6. በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚያስፍልገዉን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፍል ከደጎሎ ከተማ መ/ውሃ/ፍሳ/አገ/ድርጅት ከቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የዋጋ ማቅረቢያ መረጃ አሟልቶ በእያንዳንዱ በፖስታ አብሮ በማሸግ እያንዳንዳቸዉ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ስም ፊርማ ማህተም በማድረግ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ መሂ 1 ማስያዝ ያለባቸዉና የአሸናፊነት ደብዳቤ በደረሳቸዉ በ5 የስራ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ዉል መዉሰድ አለባቸዉ፡፡
  9. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16 ኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚያዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ድርጅቱ በጨረታዉ የሚገዙ እቃዎች ላይ 20 በመቶ ጨምሮና ቀንሶ መግዛት መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. ማንኛዉም ተጫራች ግዥዉ በጥቅል (ሎት) መሆኑን አዉቆ ለእያንዳንዱ እቃ ዝርዝር ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ የተዘረዘሩ እቃዎችን በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉድቅ ይሆናል፡፡ እንድሁም አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሽነፋቸዉን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ገቢ ካላደረጉ ክፍያ የማይፈጸም መሆኑ ይታወቅ፡፡
  12. ናሙና ማቅረብ ያለባቸዉ እቃዎችን አሸናፊዉ ተጫራች ዉል ከመዉሰዱ በፊት ባሉት 5 ቀናት ዉስጥ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  13. አሸናፊዉ ተጫራች ዉል በወሰደ በአንድ ሳምንት ዉስጥ እቃዉን ገቢ አድርጎ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል፡፡ ለስራዉ የሚያስፈልጉ የቀን የጉልበት ሰራተኞችንም ማመቻቸት አለበት፡፡
  14. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዥ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 35 25 474 7 /09 19 97 15 20 /09 43 74 58 58 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደጎሎ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here