የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት አገልግሎት ለመግዛት በሎት ተኝቶ ታካሚዎች የበሰለ ምግብ አቅርቦት ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ ፈቃድ ያላቸውን ነጋዴዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለአንድ ዓመት ውል በመያዝ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ እንዲሳተፍ ይጋበዛሉ፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ በዘመኑ የታደስ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤ የምግብ አገልግሎት ሰጭ ድረጅቶች ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆነቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፋ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. የበሰለ ምግብ ዓይነትና ዝርዝር ከጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ ከተዘረዘሩት አይነቶች ውስጥም የአንዱን ምግብ አይነት ሳይሞላ ቢቀር ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
3. የመጫረቻ ሠነዱን ፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ፋይናስ የሥራ ሂደት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ በግዥ ፋንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በተጠቀሰው ቀን ውስጥ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሽህ ብር) በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 80,000.00 (ሰማኒያ ሽህ ብር) በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥረዝ ድልዝ ሳይኖረው በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሰረት በመሙላት የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም ማድረግና ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በሆስፒታሉ ግዥ ፋይናስ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ 04/02/2017 ዓ.ም እሰከ 18/02/2017 ዓ.ም በግዥ ፋይናስ ቢሮ ክፍል ገቢ መደረግ አለበት፡፡
9. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ይሆናል፡፡
10. ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናስ ከፍል ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
11. ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
12. የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. ለመለጠ መረጃ በስ.ቁ 058 775 10 16 በመደወል ማግኝት ይችላሉ፡፡
የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል