በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ  ማስታወቂያ

0
100

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2018 በጀት  ዓመት  ሎት 1. የተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅርቦት፣ ሎት 2. የሆስፒታሉን ህንፃ የሪኖቬሽን ስራ ደረጃ ስድስት እና በላይ የሆኑ ተቋራጮችን እንዲሁም ሎት 3. የደህንነት ካሜራ ግዥ  በግልጽ  ጨረታ አወዳድሮ   መግዛት  ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅርብ የሚችሉ እና በሎት ሁለት ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች የብቃት ማረጋጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት እና ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ ክሊራንስ   ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ኮፒ  ከጨረታ  ሰነዱ ጋር አያይዘው  ማቅረብ  ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር  መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)  እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር   የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ  ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3  መዉሰድ የሚቻል ሲሆን ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  እስከ 15ኛዉ ቀን ድረስ እስከ 11፡30  ብቻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በልዩ ልዩ ምክንያት በሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ያልታገዱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በአማርኛ ቋንቋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር ያካተተ ሆኖ የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ  የድርጅቱ ክብ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት  ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ  ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅርቦት ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ሲሆን ለሎት ሁለት እና ለሎት ሶስት ግን የሞሉትን ጠቅላላ ድምር አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ  (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ገቢ በማድረግ የደረሰኙ ኦርጅናል ከፖስታው ውስጥ  አብሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከታወቀ ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅርቦት ብር 400,000 /አራት መቶ ሽህ ብር/ ሲሆን ለሎት ሁለት እና ለሎት ሶስት ግን ያሸነፉበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና  ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት  ሆኖ ባይገኙ  ግን ፕሮግራሙ  የማይስተጓጎል ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት  ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው  የመንግስት የሥራ ቀን  በተጠቀሰው  ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. አሸናፊ የሚለየዉ  በሎት   ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ  በሙሉ  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 827 04 27 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here