በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
59

በደቡብ ወሎ ዞን የጃማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተራድኦ በጀት ተጫራች ሎት 1. እድሳት እና ጥገና በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ለሚመለከተዉ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  6. ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ መሰረዝ መደለዝ ከጨረታዉ ዉድቅ የሚያደርግ መሆኑን አዉቀዉ በጥንቃቄ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ሎት እድሳት እና ጥገና ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) እየገዙ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  9. እድሳት ጥገናዉን በተመለከተ ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ስራ ተቋራ (GC) መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  10. አሽናፊዉ ተጫራች ያሸነፈውን እድሳት እና ጥገና በስፔስፊኬሽን መሠረት ሰርቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩ የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ መሂ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ አሸናፊ ድርጅት የአሸነፉበት ደብዳቤ በተፃፈለት በ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውል መዉሰድ አለባቸዉ፡፡
  12. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ኦርጅናል ፖስታ በጥንታቄ ማሽግ በጃማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግ/ፋ/ን/አስ/ደ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. አሸናፊዉ ድርጅት የአሽነፋቸዉን ጨረታዎች በሆስፒታሉ በኩል ዉል የመዉሰድ ግዴታ አለበት፡፡
  14. አሸናፊዉ ድርጅት የአሽነፋቸውን እድሳትና ጥገና ዉል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ የውል ገደቡ ከማለቁ በፊት የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ የመውጫ ቀነ ገደቡ ካለፈ የግዥ መመሪያ በሚፈቅደዉ መሰረት 01 በመቶ በተከታታይ ለ10 ቀን የሚያስቀጣ እርምጃ የሚያስወስድ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
  15. በሆስፒታሉ በጨረታ የሚሰራ እድሳት እና ጥገና ላይ ብዛት የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛዉ ቀን ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ) በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ የሚቀጥለዉ የሥራ ቀናት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ የመክፈቻ ሰዓቱ ከደረሰ ቢገኝም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  17. ማንኛውም ተጫራች ስራዉ በጥቅል (ሎት) የሚፈፀም መሆኑን አውቆ ለእያንዳንዱ ዝርዝር እቃዎች መሙላት ይኖርበታል፡፡ የተዘረዘሩት ግንባታዎች ክፍያ በተመለከተ በመመሪያው መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  18. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 033 226 04 91 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  19. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

የጃማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here