የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና /ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ማለትም ገንዘብ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም፡- ሎት 1 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የመኪና ጎማ፣ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ እንዲሁም ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ለባህል ቡድኖች የሚያገለግል) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የእቃዉን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ጎ/ቆ/ወ/ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥዉ ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ (በሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊቱን ከተገለፀ በኋላ የዉል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋዉን ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና /ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከታህሳስ 20 2018 ዓ.ም እስከ ጥር 05/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥር 05/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታውን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በቀን ጥር 05/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት። ሆኖም ሥርዝ ድልዝ ካለ ስለ መስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ 20 በመቶ መጨመር መቀነስ ይችላል እና ማንኛውም ተጫራች ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ሳምፕል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን እቃውን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ሊያቀረብ ነው፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና /ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 556 75 58 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት

