በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
89

በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው የአዊ ልማት ማህበር በዚገም ወረዳ ሶሪት ቀበሌ ያመረተውን ሰብል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማሟላት አለባችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግዥው ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ጠቅላላ ዋጋውን ታክሱን ጨምሮ በመሙላት በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ጨረታ ማስከበሪያው ለየብቻ በመለየትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በጋዜጣ በወጣው በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  7. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊው ድርጅት አስር በመቶ ውል ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስላቸው አሸናፊው ውል ከያዘ በኋላ ነው፡፡
  10. ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 227 03 62 /058 227 11 88 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአዊ ልማት ማህበር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here