በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
79

የመገናኛ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ዩኒዬን ኃ.የተ  በደ/ጎንደር ዞን በደ/ታቦር ከተማ በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ የሚገኝ ሲሆን  በመገጋዘን ውስጥ የሚገኘውን ብዛት 258.41 ኩ/ል ከደረጃ በታች የሆነ ማዳበሪያ ማለትም ዳፕ 126.41 ኩ/ል ፣ዩሪያ 96 ኩ/ል፣ ኤንፒኤስ ቢ /NPSB/ 36 ደብረታቦር የዩኒየኑ ማራገፊያና ማሰራጫ ጣቢያ የሚገኝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች /ግለሰቦች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መጫረት የሚችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ መገናኛ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ስማቸውን ፣ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸዉን ማስፈር አለባቸዉ፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተሸጦ በ7ኛው ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 7ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎችን አይነት ፣መጠንና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በመክፈል /በመግዛት የመወዳደሪያ ዋጋ ፣ስማቸውን ፣ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-5 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የገዛውን ማዳበሪያ ሙሉ በሙሉ ማንሳት የሚችል፡፡
  8. አሸናፊዉ በተለየ በ5 ቀን ዉስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉስድ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች የግብዓት ማስጫኛ ዋጋ ይከፍላል፡፡
  10. አሸናፊ የሚለየው በተወዳደረበት ጠቅላላ ዋጋ ይሆናል፡፡
  11. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የርክክብ ቦታ ማዳበሪያው ባለበት ደ/ታቦር መጋዘን ሲሆን  ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ምርቱን የማንሳት ግዴታ አለበት፡፡
  13. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በዚህ የተጫራቾች መመሪያ ያልተካተቱ ሌሎች ጉዳዮች በተሻሻለዉ የህብረት ሥራ ማህበራት የግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 58/2015 ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 28 64 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የመገናኛ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ዩኒዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here