በድጋሜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 08/2016

0
136

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የዋናዉ ቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ ኮረኔስ እና ቴሌቬዥን ህንጻ ዉስጥ የሚገኙት ኮርኔስ ለማሰራት የህንጻ እና የጠቅላላ ተቌራጮችን ከደረጃ 7 እና በላይ የሆኑ ብቻ የሚሳተፉበት በግልጽ ጨረታ ዘዴ በበኩር ጋዜጣ አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራት ይፈለጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የስራና ከተማ ልማት የደረጃ ማረጋገጫ ሰርተፌኬት፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ሰርተፍኬት፡ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21/ሃያ አንድ/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104 300/ሶስት መቶ/ ብር ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል፡፡ ሰነዱን በጥንቃቄ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት የፋይናስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡ በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸዉ መ/ቤት የቅርብ ጊዜ ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው በ22ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥናንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ሂደት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተመሰከረለት ቼክ/ስፒኦ/፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት 22ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡3ዐ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የግንባታ ስራዉ ዓይነት፣ ብዛት እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 በፋክስ 058 320 7069 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here