በድጋሜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
96

በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደ/ቦር ከተማ የሚገኘዉ የመገናኛ የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኔዬን ኃ.የተ. በሎት /በምድብ/:- ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባቶች፣ ሎት 5 የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 6 የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ሎት 7 የእህል ሚዛን፣ ሎት 8 የዉሃ ታንከር፣ ሎት 9 ጀኔሬተር በድጋሜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላል፡-

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /2%/ በመገናኛ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
  3. የግዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፣
  4. ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎችን አይነት፣ መጠንና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በመክፈል/በመግዛት የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፣
  5. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-4 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት በ5 ቀን ዉስጥ የአሸነፈበትን እቃ /ንብረት/ ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ /10%/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉስድይኖርባቸዋል፡፡
  7. አሸናፊው የሚለየው በሎት /በምድብ/ ዋጋ ይሆናል። ከሎት ውስጥ የአንዱን ዕቃ ዋጋ ካልሞሉ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።
  8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ7ኛው ቀን  ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ ፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች የአሸነፉትን እቃ /ንብረት/ ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን በደ/ታቦር ከተማ ከሚገኘው መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችል፣
  10. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /0581419927 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡

መገናኛ ሁለገብ የገበ/ህ /ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተወሰነ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here