በድጋሜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
153

የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል አድራሻ ባሕር ዳር ዓባይ ማዶ ቀበሌ ሕዳር 11 ከኮበል ኢንዱስትሪ ጎን ሲሆን ሎት 1. የብስክሌት መለዋወጫ፣ ሎት 2. የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 3. የመኪና ዘይት እና ቅባቶች እንዲሁም  ሎት 4. የፅዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡-

  1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት /ቲን/ ያላቸዉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የዋጋውን ጠቅላላ አንድ በመቶ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ዋጋቸው ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  5. ለማንኛውን ግዥ ለዕቃዎች 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ እና ለአገልግሎት 3,000.00 /ሦስት ሽህ ብር/ እና ሁለት በመቶ የቅድመ ግብር ተቀንሶ ይቀራል፡፡
  6. ማዕከሉ ከሚገዛው ዕቃ የዋጋውን ሀያ በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለው፡፡
  7. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን አስር በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ዋጋ በመሆኑ ሁሉንም የተዘረዘሩት ዕቃዎች መሞላት አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 60 /ስልሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. የእቃዎችን አይነት /ሞዴል /ማዕከሉ ድረስ በአካል መጥቶ ማየት ይቻላል፡፡
  12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ታሽጎ ወዲያው በዕለቱ በ4:00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  13. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ከማዕከሉ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
  14. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ለወደፊትም ከመንግስት ግዥ እንደማይሳተፉና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያም የሚወረስ ይሆናል፡፡
  15. ማዕከሉ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 321 54 82/058 820 97 84 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 5 ቀርቦ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሀድሶ አገልግሎት ማዕከል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here