በ “ፑል አፕ” ባለ ክብረወሰኗ

0
11

የ32 ዓመቷ አውስትራሊያዊት ወጣት የፓሊስ መኮንን በአንድ ሰዓት ውስጥ 733 “ፑል አፕ” በመስራት በ2016 እ.አ.አ በኤቫ ክላርክ የተመዘገበውን በስምንት በመብለጥ ክብረወሰን መስበሯን ዩፒአይ ድረገጽ ባለፈው ሳምንት ለንባብ አብቅቶታል፡፡

ጄዲ አንደርስን አዲስ ክብረወሰን ያስመዘገበችው በ2016 በአውስትራሊያዊቷ ኤቫ ክላርክ  725 “ፑል አፕ” በደቂቃ  የተመዘገበውን በስምንት በልጣ በ733 አዲስ ክብረወሰን በመያዟ ነው፡፡

ወጣቷ ቀደም ብሎ በ24 ሰዓታት ፑል አፕ በመስራት በሌላዋ አውስትራሊያዊት ኦሊቪያ ቪንሰን የተያዘውን 7,079 ክብረወሰን ለመስበር አቅዳ ስትለማመድ መቆየቷን  ተናግራለች፡፡ ሆኖም ባለፈው 2024 ሚያዚያ ወር ባደረገችው የመጨረሻ ሙከራ በ12 ሰዓታት ውስጥ 3500 “ፑል አፕ” ሰርታ የእግር ጡንቻ ጅማት መሰንጠቅ  ስለደረሰባት  በሀኪም የተሰጣትን የእረፍት ጊዜ ጨርሳ የአንድ ሰዓት ክብረወሰን ለመያዝ መዘጋጀቷን ነው የገለፀችው፡፡

ጄዲ አንደርሰን በኤቫ ክላርክ በክብረወሰን የተያዘውን 725 ማሻሻል ከባድ እንደ ሚሆንባት በማሰብ  ጠንካራ  ልምምድ  ማድረጓን ተናግራለች፡፡ ከቀዳሚዋ የአገሯ ልጅ ከተመዘገበው በጣም ባያርቅም በጠባብ ልዩነት ለመብለጥ ማለሟንም ነው የጠቆመችው፡፡

ያለመችውን ለማሳካት ቀደም ብሎ ከተያዘው ክብረወሰን ምን ያህል አብላጫ ማስመዝገብ እንዳለባት በግልፅ የተቀመጠ ቁጥር አልነበራትም፤ በቃ በጥቂት አብላጫ  መብለጥ ብቻ እንጂ፡፡

በመጨረሻው እለት ጄዲ ቀደም ብሎ ህመም የነበረባቸው እግሮቿ እና እጆቿ መተሳሰር፣ የአለመታዘዝ ስሜት እንደተሰማት እና እልህ አስጨረሻ ሙከራዋን እንደገፋችበት አልሸሸገችም፡፡ እንዳለመችውም ክብወረሰን የማስመዝገብ ህልሟ እውን ሆነ፤ ለአስር ዓመታት ያህል ከተያዘው ስምንት ፑል አፕ በመብለጥ በ733 ባለክብረወሰን ለመሆን መብቃቷም ነው ለንባብ ያበቃው፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here