በአዊ ሔረሰብ አስተዳር መምሪያ በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የእንጅባራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ከውስጥ ገቢ በጀት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 ህትመት፣ ሎት 2 መድኃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መጫረት የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የዋጋውን ጠቅላላ አስር በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የመድኃኒትና ህትመት አይነቶችን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል እን/ጤ/አጠ/ጣቢያ ግ/ፋ/ቡ ቢሮ ቁ 35 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም እን/ጤ/አጠ/ጣቢያ ደረሰኝ በመ/ሂ1 ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ፖስታ በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በእን/ከ/አስ/ጤ/አጠ/ ጣቢያ ግ/ፋ/ቡ/ ወይም ቢሮ ቁጥር 35 ጨረታው በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/ቡ ቢሮ ቁጥር 35 ጨረታው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡
- በሎት 1 ላይ የሚወዳደር አንድ ተጫራች በዚሁ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የህትመት አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም፡፡ በዚሁ ምድብ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት መስፈርቱን በማሟላት ከጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፏቸውን ህትመቶችንና የመድኃኒት እና የህክምና መሳሪያዎችን እን/ከ/አስ/ጤ/አጠ/ጣቢያ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ እን/ከተ/አስ/እን/ከ/አስ/ጤ/አጠ/ ጣቢያ ግ/ፋ/ቡ/ ቢ.ቁ 35 24 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቀጥር 058 227 01 65 /09 18 13 99 85 /09 18 67 04 42/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የእን/ከ/አስ/ጤ/አጠ/ጣቢያ እንደ በጀት አቅሙ ሃያ በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በሎት 2. ወይም በመድኃኒት እና የህክምና መሳሪያ የሚወዳደር ተጫራቾች አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ የመድኃኒት እና የህክምና መሳሪያ ዋጋ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ:- የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የእንጅባራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ