ቨርጂን አይላንድ ብሔራዊ ፓርክ

0
13

ቨርጂን አይላንድ ብሔራዊ ፓርክ 14,737 ሄክታር ወይም 59.64 ኪሎ ሜትር ስኩዌር የየብስ እና የውቅያኖስ ቀጣናን አቅፏል፡፡ መገኛው በአሜሪካ ስር በምትገኘው ቨርጂን ደሴት እና አዋሳኝ የውቅያኖስ ክልል ነው፡፡

ፓርኩ በነሀሴ 2/1956 እ.አ.አ ነው የተመሰረተው፡፡ በበላይነት የሚያስተዳድረው ብሔራዊ የፓርኮች አገልግሎት ነው፡፡ ከፓርኩ ጠቅላላ ስፋት 9087 ሄክታሩ የብስ ሲሆን 5650 ሄክታሩ አዋሳኝ የውቅያኖስ ቀጣና ነው፡፡

በፓርኩ 740 የዕፅዋት ዝርያዎች መገኘታቸውን ድረ ገፆች አስነብበዋል፡፡ በደሴቷ ዳርቻ የ”ትሮፒካል” ሞቃት ቀጣና ደንን ለብሷል፡፡ ደኑም ለተለያዩ የዱር እንስሳት በመጠለያነት ያገለግላል፡፡

በፓርኩ 140 የዓዕዋፍ፣ 302 የዓሳ፣ 7 የ”አምፊቢያንስ” 22 አጥቢ እንስሳት ዝርያዎች ተመዝግበዋል፡፡ በተጨማሪም 50 የሚጠጉ የባህር ዛጐል ወይም “ኮራል ሪፍስ” መገኘታቸው የባህር ጠላቂዎችን ቀልብ የሚስብ ቦታ አድርጐታል፡፡

ቨርጂን አይላንድ በዓመቱ 55 ኢንች አማካይ ዝናብ ያገኛል፡፡ ከፍተኛው የዝናብ መጠንም ከነሀሴ እስከ ህዳር ባሉት ወራት ነው የሚጥለው፡፡

የፓርኩ ቀጣና ዓየር ንብረት አማካይ  18 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የዓየር ንብረቱ በክረምት እና በጋ ወራት መካከል ጠባብ ልዩነት ነው ያለው፡፡ የባህሩ ቀጣና ግን ዓመቱን ሙሉ ሞቃት መሆኑን ድረገፆች አስነብበዋል፡፡

ብሔራዊ ፓርኩ ለጐብኚዎች በማንኛውም ሰዓት  ክፍት  መሆኑ  ከሌሎች  ልዩ      ያደርገዋል፡፡

በፓርኩ ከፍተኛ ጐብኝዎች  የተመዘገበበት 2018 እ.አ.አ ሲሆን ቁጥሩም 12,287  ነው፡፡

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ጐስ ኦይሊቭ ዶትኮም፣ ሴቭ ኘላኔት ዶት ኦርግ ድረገፆችን እና ዊኪፒዲያን ተጠቅመናል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here