ሀሉም ወገኖች ሰብአዊ የተኩስ ማቆም
አድርገው ወደ ውይይት እንዲያመሩ
ኢሰመኮ ጠየቀ
በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል
ክልሎች በጥቅምት እና በኅዳር ወራት
2016 ዓ.ም በርካታ ሰዎች መገደላቸውን
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
(ኢሰመኮ) አስታውቋል። ኮሚሽኑ ሰሞኑን
ባወጣው መግለጫ በአማራ፣ በኦሮሚያ
እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከሁለት
ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በታጣቂዎች
በተፈጸሙ ጥቃቶች እና በተከሰቱ ግጭቶች
በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ነው
ያስታወቀው።