ተፈጥሯዊ ሽታ

0
154

ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

 ተፈጥሮን መመልከት ከሚያስገኛቸው የጤና ጥቅሞች ጋር ሲነፃፀር ከተፈጥሯዊ አካባቢ የሚነሳ ጥሩ ሽታ በጤንነት ላይ የሚያሳደረውን ተጽእኖ በውል መለየት የሚያስችል ተግባራትን እንዲያከናውኑ ለተመራማሪዎች ጥሪ መቅረቡን ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ  አስነብቧል::

በአሜሪካ የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ በመረጃ ምንጭነት እንዳስነበበው እስከ አሁን የተካሄዱ በርካታ ጥናት እና ምርምሮች ተፈጥሮን መመልከት የአካል ደህንነትን እንደሚያሻሽል አመላክተዋል::

ከዚህም ባሻገር ከየሀገራት የተሰባሰቡ የተመራማሪዎች ቡድን ከተፈጥሮ የሚነሳው ጥሩ መዓዛ ያለው ሽታ  በጤና ላይ የሚኖረው ተጽእኖ በጥልቀት እንዲጠና ጥሪ አቅርበዋል:: ለዚህም በምክንያትነት ያነሱት በማሽተት ከተፈጥሮ የሚገኘው ጥቅም  በጥልቅ ጥናት አለመለየቱን ነው::

በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ እና የደን ሳይንስ ረዳት ፕሮፌሰር ግሪጐሪ ብራትማን በበኩላቸው ሰዎች ሽታ በበዛው ዓለም ውስጥ  ይኑሩ እንጂ በስሜት እና በባህሪ ላይ የተፈጥሮ መልካም መዓዛ ያላቸው ሽታዎች  ምን ያህል ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ ብዙም አለመታወቁን አስረድተዋል::

የሰዎች የማሽተት ስሜት በአንድ ጊዜ በርካታ ውስብስብ የኬሚካል ውህዶችን ይቀበላል:: በአፍንጫ ውስጥ ባሉ መለያዎች የተቀበላቸው ውህድ ሽታዎች መቼ? የት? እንዴት? ሰዎችን ሊነኩ እንደሚችሉ ግን አለመለየቱንም ነው ፕሮፌሰሩ ያረጋገጡት::

በቀጣይ የሚደረግ ገብ ጥናት በአንድ የትምህርት መስክ የተካኑ ምሁራንን ብቻ ሳይሆን  የየመስክ ሊቃውንትን ጣልቃ ገብነት እንደሚጠይቅ ነው የተገለጸው።

በቀጣዩ ምርምር እና ጥናት ነባር እውቀትን፣ የሰው ዘር ጥናት ፣ የከባቢ ዓየር ኬሚስትሪ፣ የደን ሥነ ምህዳር እና የሥነ አእምሮ ተመራማሪዎችን ማካተት  እንደሚገባውም ተጠቁሟል።

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here