ተፈጥሯዊ ቀለምን የሚቀይረው

0
136

በጥቁር ውሻው ላይ አልፎ አልፎ ጠብ ጠብ ያለ ነጭ ቀለም ተመልክቶ ወደ እንስሳት ህክምና ያመራው አሳዳሪ በምርመራ “ቫይቲልጐ” በተባለ በሽታ መጠቃቱ ከተነገረው ከሁለት ዓመታት በኋላ ሙሉ በሙሉ ወደ ነጭነት መቀየሩን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ከሳምንት በፊት ለንባብ አብቅቶታል::

እንደ አወሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2021 የጥቁር ውሻው ባለቤት ወይም ባለንብረት ገና ነጭ ቀለም ያለው ፀጉር አልፎ አልፎ በውሻው ቆዳ ላይ ሲመለከት ወደ ህክምና ጣቢያ ይወስደዋል::

በምርመራ ውሻው “ባይቲልጐ” በተሰኘ በሽታ መጠቃቱ ይነገረዋል:: በሽታው በውሻው ጤና ላይ እክል እንደሚያስከትል እና ሁኔታውን እንዲከታተለው ይመክሩታል –  የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች::

“ቨስተር” የተሰኘው ውሻ አሳዳሪ ማት ስሚዝ ወደ ህከምና ጣቢያ ከወሰደው ከዘጠኝ ወራት በኋላ ፊቱ ነጭ ቀለም የተረጨበት እንደመሰለ ያስታውሳል::

የውሻውን የቆዳ የቀለም ለውጥ በየጊዜው ፎቶ በማንሳት ለማህበራዊ ሚዲያ ያጋራው ማት ስሚዝ የማይታመን መሆኑን በርካታ ተመልካቾች አስተያየታቸውን ያስነበቡ መሆናቸውንም ተናግሯል::

የውሻው አሳዳሪ የሚወደውን የቤት እንስሳ በየጊዜው ፎቶ ግራፍ እያነሳ ለውጡንም መሰነድ  ችሏል:: አስገራሚው “ባይቲልጐ” በተሰኘው በሽታ የውሻው ሙሉ ፀጉር፣ የቆዳ እና የዐይኑ ቀለም ሳይቀር መቀየሩንም ነው ለተመልካች ያጋራው::

ከሁለት ዓመት በፊት ጥቁር የነበረው “ቨስተር” አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ነጭ መሆኑን ልብ ይሏል- ተፈጥሯዊ ቀለምን በሚቀይረው “ቫይቲልጐ” በሽታ::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here