ብዙ ጊዜ ሰዎች አዲስ ነገር ለማየትና ለማወቅ፣ ከነበሩበት አካባቢ የተለየና አዲስ ልምድና ተሞክሮ ለመቅሰም፣ ባላቸው ላይ ለመጨመር አንዳንዶች ደግሞ ዓለምን ለማሰስ ካላቸው ጥልቅ ፍላጎት የመነጨ ከሀገር ሀገር እየተዘዋወሩ ይጎበኛሉ::
አንዳንዶች ለራሳቸው የጽሞና ጊዜ ለመስጠት ከሚኖሩበትና ከተለመዱት አውድ ወጥተው በአዲስ አካባቢን እየጎበኙ ለራሳቸው ጊዜ ለመስጠትና የዓዕምሮ ረፍት ለማግኘት መዘዋወርን ይመርጣሉ::
ሌሎች ለስራ፣ ለህክምና፣ ለትምህርት፣ ለንግድ አሊያም በጋብቻ፣ ዘመድ ለመጠየቅና ለመሳሰሉት ለአጭር ወይም ለረጅም ጊዜ ከአንድን ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሊንቀሳቀሱና ሊጐበኙ ከዚህ በተጨማሪም ይችላሉ::
በጣም የተለዬና የሚስብ ተፈጥራዊ ውበትን ጨምሮ ተራሮች፤ ለየት ያለ የመሬት አቀማመጥ የወንዝ ዳርቻዎች፤ ደኖች፣ ሙዚየሞች፣ ሀውልቶች፣ የተለየ ፌስቲቫል የስፖርታዊ ውድድሮችና ፌስቲሻሎችና የመሳሰሉትን በዋናነት መጎብኘት ምርጫቸው የሆኑ በርካታ ቱሪስች አሉ::
የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ማራዘምና ከዚያ ገቢን ማግኘት ደግሞ የመዳረሻዎቹ ጉዳይ ነው::
ጎብኝዎች አንድን ሀገር ለመጎብኘት እንደቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጡት ጉዳይ አለ:: የደህንነት ዋስትና ያለበትና ከስጋት ነጻ ሆኖ ለመዝናናትና ለመቆየት የሚመች መሆን፣ በአቅራቢያው ምቹና ፈጣን የሆነ መንገድና መጓጓዣ መኖር፣ ቢታመሙ የህክምና እርዳታ በፍጥነት ማግኘት የሚችሉበት ቦታ፣ ደረጃውን የጠበቀና ምቹ የሆነ ማረፊያ፣ ሌሎች አገልግሎቶች መስጫ ለምሳሌ ሆቴልና ሬስቶራንትን ጨምሮ ገበያና ለጎብኝዎች ስለቦታው መረጃ የሚሰጥ ሰው መኖርና የተደራጀ የጎብኝ መረጃ የሚሰጥበት ማዕከል መኖር የሚሉት ከበርካታ መስፈርቶችና መለኪያዎች መካከል ይገኙበታል::
በየጉብኝት መዳረሻ ቦታዎች አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ምቹነትና እንግዳ አቀባበል እንዲሁም ቤተሰባዊ የሆነ አቀራረብ የጎብኝን የቆይታ ጊዜ ለማራም ከምክንያቶቹ አንዱ ነው::
ይህ ደግሞ አንድ ጎብኝ ከሀገሩ ከመውጣቱ በፊት ከሚጎበኘው ቦታ እኩል የሚጎበኙ አካባቢዎች ስለሚኖሩ ሰዎች ባህሪ በሌሎች ቱሪስቶች ከዚህ በፊት የተሰጣቸው በጎ አስተያየትና አድናቆት ለጉብኝት እንደ ምክንያትነት ይጠቀሙበታል:: ጎብኝ ሲመጣ ሀገርን እንደሰው በአካል አያገኘውም:: “መልካም ስም ከመልካም ሽቶ ይበልጣል” እንደሚባለው በመልካም አቀባበል ተቀብሎ መሸኘትም ሆነ መልካም መሆን ለሌላ ጉብኝት እንደቀብድ ነው::
የቱሪዝም ዋና አላማው የጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ በማስረዘም ገቢንም መጨመር መቻል ነው:: የጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ ለማስረዘም የጉብኝት ቦታዎችን ማስፋት፣ ፍላጎት እና አቅርቦትን ማጣጣምና ደረጃቸውን ማስጠበቅ መቻል ያስፈልጋል::
ወደ ክልሉ የሚመጡ የጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ ለማርዘም የመስህብ ሀብቶችን
በተለይም የቱሪዝም ዘርፉ ለኢኮኖሚው የሚያበረክተውን ድርሻ ለማሳደግ የአማራ ክልል የ25 ዓመት የልማት አሻጋሪ ዕቅድን ቀርጾ ወደ ሥራ ሲገባ ቱሪዝም አንዱ የትኩረት መስክ ነው::
ክልሉ ካለው በርካታ የመስህብ ሃብት አንጻር በየዓመቱ ከጎብኝዎች የሚገኘው ገቢ በቂ አይደለም:: ባይባልም ወደመዳረሻ የሚወስዱ መንገዶችን በማስተካከል፣ መዳረሻ ቦታዎችን ምቹና ንጹህ በማድረግ እንዲሁም በየመዳረሻዋች ቀልጦፋ አገልግሎት በመስጠት ተመራጭ መሆንና ገቢውንም ማሳደግ ይቻላል::
በኲር የመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም