በሀገራችን አብዛኛው አካባቢ ምክንያቱ
ባይታወቅም የኢንፍሉዌንዛ በሽታ መከሰቱ
ይታወቃል:: በሽታው ከጉንፋን ጋር ተመሳሳይነት
ያለው ሲሆን አብዛኛው ታማሚ ተመሳሳይ
ምልክቶችን ያሳያል:: ማሳል፣ ማስነጠስ፣
ትኩሳት፣ ቁርጥማት፣ የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት
እና መሰል ነገሮች የሕመሙ ምልክቶች ናቸው::
ይሄው ሕመም ፆታ እና ዕድሜ ሳይለይ
ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች በማጥቃት
ላይ ይገኛል:: ለአብነት በባሕር ዳር ከተማ
ውስጥ በሚገኙት ሁሉም የጤና ማዕከላት
ውስጥ አብዛኛውን የታማሚ ቁጥር የሚይዙት
የዚሁ ጉንፋን መሰል በሽታ (ኢንፍሉዌንዛ)
ታማሚዎች ናቸው::
የኔ ትዝብት የኢንፍሉዌንዛ በሽታን
እንዴት መከላከል ተሳነን? በሽታውን ቀድመን
ለመከላከል ማድረግ ያሉብንን ጥንቃቄዎች
ማሳወቅ ወይም ከበሽታው በኋላ መደረግ
ስላለባቸው ጉዳዮች ማሳወቅ አይደለም፤
ይልቁንም የበሽታውን መስፋፋት ተከትሎ
መድኃኒት ቤቶች ለኅብረተሰቡ የሚሸጧቸውን
መድኃኒቶች የሀኪም ትዕዛዝ አልባነት
ታዝቤያለሁ::
አንድ ሕክምና ፈላጊ ግለሰብ የራሱን ሕመም
ለመገመት የሚያስችሉት በርካታ ምልክቶች
ቢኖሩትም ትክክለኛ ሕመሙን ለማወቅ ግን
የግድ የባለሙያ እገዛ ያስፈልገዋል:: የራስ ሕመም
የተሰማው ሰው ሁሉ ራሱን ታሟል ማለት
እንደማይቻል ሁሉ ሰውነቱን የሚያንቀጠቅጠው
ሰውም በወባ ትንኝ ተጠቅቷል ብሎ መደምደም