በህንድ አግራ ውስጥ የሚገኘው ታጅ ማሃል በአለም አቀፍ ቅርስነት ከሚታወቁት ድንቅ ስራዎች አንዱ ነው። ይህ አስደናቂ ነጭ እብነበረድ መካነ መቃብር ለሙግሀል ንጉሥ ተወዳጅ ባለቤታቸው ሙምታዝ ማሃል መታሰቢያ በሙጋል አፄ ሻህ ጃሃን የተሰራ ነው።
ታጅ ማሃል በአስደናቂ ውበቱ ብቻ ሳይሆን በታላቅ ታሪኩ እና በረቀቀ የኪነ ህንፃ ንድፉ ታዋቂ ነው። ታሪኩ ከንጉሡ ፍቅረኛ በወሊድ ምክንያት መሞት በኋላ ለመታሰቢያ ይሆናት ዘንድ እጅግ ይወዳት የነበረው ባለቤቷ ያሰራው ነበር። ሰኔ 17 ቀን 1632 ዓ.ም እንደሞተች የሚነገርላት ሙንታዝ ማሀል ከመሞቷ በፊት የመቃብር ስፍራ እንዲገነባላት በተናዘዘችው መሰረት የተገነባ እጅግ የዘመናችን ድንቁ የሰው ልጅ የእጅ ስራ ውጤት ነው።
በፍቅረኛው ሞት ዓለሙ የጨለመበት ንጉሥ ሻን ጃሃን በሀዘን መብዛት በአጭር ጊዜ እንዳረጀ ይነገራል። እናም ቀሪው ዘመኑን እጅግ ስለሚወዳት ውድ ፍቅረኛው ውዱን የዓለማችንን የመቃብር ስፍራ በማስገንባት አሳልፏል። ሙንታዝ ከሞተች ከስድስት ወራት በኋላ ግንባታው የተጀመረው ታጅ ማሀል አስራ እልፈት ዓመታትን ፈጅቷል።
ታጅ ማሃል በ1623 ዓ.ም በአምስተኛው የሙጓል ንጉሠ ነገሥት ሻህ ጃሃን የተሾመው ባለቤታቸው ሙንታዝ ማሃል በወሊድ ወቅት ከሞቱ በኋላ ነው። ግንባታው በ1624 ዓ.ም ተጀምሮ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የቀጠለ ሲሆን ዋናው መካነ መቃብር በ1635 ዓ.ም ተጠናቀቀ እና በዙሪያው ያሉት ህንጻዎች እና የአትክልት ስፍራዎች በ1653 ተጠናቀዋል።
ግንባታው ከሙጋል ኢምፓየር እና ከዚያም ባሻገር በሺዎች የሚቆጠሩ የእጅ ባለሙያዎችን አሳትፏል። ምንም እንኳን ፕሮጀክቱ በርካታ ችሎታ ያላቸው ዲዛይነሮችን እና ግንበኞችን ያሳተፈ የትብብር ውጤት ቢሆንም ዋናው አርክቴክት ኡስታዝ አህመድ ላሀውሪ እንደሆነ ይነገራል። ቁሳቁሶች ከተለያዩ ክልሎች የተገኙ ሲሆን ነጭ እብነ በረድ በራጃስታን ውስጥ ከማክራና፣ ከፑንጃብ፣ ከቻይና፣ ከቲቤት፣ ከአፍጋኒስታን እና ከስሪላንካ በዝሆኖች ተጓጉዘው የመጡ የከበሩ ድንጋዮች እና ሌሎችም ጥቅም ላይ ከዋሉት መሀል ይጠቀሳሉ።
የታጅ ማሃል ሕንፃው ፍጹም የተመጣጠነ እና የተዋሃዱ መጠኖች ምሳሌ ነው። ወደ 73 ሜትር (240 ጫማ) ከፍታ ያለው ማዕከላዊ ጉልላት በአራት ትንንሽ ጉልላቶች የታጠረ ነው። እያንዳንዱ የአወቃቀሩ ጎን ትልቅ የቅስት ቅርጽ ያለው በር አለው፣ ውስብስብ የአበባ እና የጂኦሜትሪክ ንድፎችን የሚፈጥሩ ውድ የከበሩ ድንጋዮች አሉ።
ታጅ ማሃል ቻርባግ ወይም ባለ አራት ክፍል የአትክልት ስፍራ በመባል በሚታወቀው ሰፊ የሙጋል የአትክልት ስፍራ ውስጥ ተቀምጧል። ይህም የገነትን እስላማዊ ጽንሰ-ሀሳብ ያመለክታል። የአትክልት ስፍራው መቃብሩን በሚያንፀባርቁ የእግረኛ መንገዶች እና የውሃ ሰርጦች የተከፋፈለ ሲሆን ይህም አስደናቂ የእይታ ውጤት ይፈጥራል።
እያንዳንዳቸው 40 ሜትር (131 ጫማ) ቁመት ያላቸው አራት ቀጫጭን ሚናሮች በተነሳው መድረክ ጥግ ላይ ተቀምጠዋል። እነዚህ ሚናራዎች የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ጊዜ ዋናውን መቃብር ለመጠበቅ በትንሹ ወደ ውጭ ዘንበል ያሉ በመሆናቸው መዋቅሩ ላይ ያለውን ትልቅነት ለመጨመር ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊ ዓላማም ያገለግላሉ።
በመቃብሩ ውስጥ፣ ማዕከላዊው ክፍል የሙምታዝ ማሃል እና የሻህ ጃሃን ሴኖታፍ ይገኛል። የውስጠኛው ክፍል በተቀረጹ ቅርጻ ቅርጾች፣ ውስብስብ በሆነው ፒዬትራ ዱራ (የእብነበረድ ሥራ) እና የቁርኣን ጥቅሶች ባሉበት ካሊግራፊ ያጌጠ ነው። በመቃብር ውስጥ ያለው ብርሃን ውበቱን በማጎልበት አስደናቂ ድባብ ይፈጥራል።
ንጉስ ሻን ጃን በወሊድ ወቅት ላለፈችው ውድ ሚስቱ መታሰቢያ የገነባው ነው። በነጭ እብን በረድ የተገነባው የታጅ መሀል ስራ አስራ አምስት አመታትን ጨርሷል። የፍቅሩን እና ሀብቱን አፍስሶበታል በሚባልለት በዚህ ቅርስ ስራ ላይ 20 ሺህ የተለያዩ ባለሙያዎች ከቱርክ እና ከኢራቅ የመጡ ባለሙያዎች እንደተሳተፉበት መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ሁለቱ ሕንፃዎች በመቃብሩ ስፍራ ላይ የሚታዩ ሲሆን በምእራብ በኩል ያለው መስጊድ ነው። ሌላው የቀድሞው ዋይት ሀውስ ነበር። ሕንፃዎቹ በአለም አቻ የሌላቸው ወሰኔ ናቸው።
በ1975 ዓ.ም በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው ታጅ ማሃል በድንቅ የኪነ ሕንፃ ንድፉ የተመለከተውን ሁሉ የሚያስደምም የሰው ልጅ የጥበብ ማሳያ ተደርጎ ይቆጠራል። አጠቃላይ ሕንፃው ያረፈበት ስፍራ 17 ሄክታር እንደሚሆን ይገመታል።
ሻን አጃንስ ንጉሱ ራሱ በእነዚህ ሕንፃዎች መገንባት ደስ ቢለውም ያጣትን ውድ ሚስቱን ሊተካለት ባይችልም ከመሞቷ በፊት የተናዘዘችውን አደራ ተወጥቷል። ሻን አጃንስ በመጨረሻም በእነዚህ ሕንፃዎች ውስጥ አሳልፏል በመጨረሻ በ74 ዓመቱ ከሞት ከሚስቱ ጎን እንደቀበረው ታሪኩ ያስረዳል።
ታጅ ማሀል በአሁኑ ዘመን በርካታ ቱሪስቶችን ከመላው ዓለም የሚጎበኙት ዘመናትን የተሻገረ አስገራሚ የዓለም ቅርስ ነው። የሕንድ ታሪክ፣ ባህል እና ማንነት መገለጫ በመሆኑ በልዩ ጥበቃ እና እንክብካቤ ተይዞ ይገኛል፣ እኛም አበቃን።
(መሰረት ቸኮል)
በኲር ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም