አህጉር አቋራጯ ጀግኒት

0
54

የ21 አመቷ ወጣት ብቻዋን በሞተር ጀልባ አትላንቲክ ውቅያኖስን 2026 ኪሎ ሜትር ተጉዛ በማቋረጧ ሦስት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ለመሆን መብቃቷን ዩፒአይ ድረ ገጽ ከሰሞኑ አስነብቧል::

የ21 ዓመቷ እንግሊዛዊት ዛራ ላክለን ከሌጐስ ፖርቹጋል መነሻዋን አድርጋ ስምንት ሜትር በምትረዝም ሞተር ጀልባ ወደ ካየን ከዚያም ወደ ፍሬንች ጉያና 97 ቀናት ከ10 ሰዓት ከ20 ደቂቃ የፈጀ ጉዞ ማድረግ ችላለች::

እንግሊዛዊቷ ዛራ ላክለን በዚህ ሁሉ ሂደት  አልፋ በዓለም አቀፍ የድንቃድንቅ መዝገብ ሦስት ክብረወሰን በስሟ አስመዝግባለች:: አንደኛው ከአውሮፓ ወደ ደቡብ አሜሪካ ያቋረጠች የመጀመሪያ ሴት በመሆኗ፤ ሁለተኛው ከአውሮፓ ወደ አሜሪካ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ብቻዋን ያቋረጠች ሴት በመሆኗ ሦስተኛው  በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ከአውሮፓ ወደ አሜሪካ ብቻዋን ያቋረጠች በእድሜ ትንሿ ሴት በመሆኗ ሦስት ክብረወሰን ማስመዝገብ ችላለች::

ወጣቷ እንደተናገረችው በየእለቱ 17 ሰዓታት በባህር ላይ ያለማቋረጥ ትጓዝ ነበር፤ ከ24 ሰዓቱ ውስጥ በእንቅልፍ የምታሳልፈው በአንድ ጊዜ ከአንድ ሰዓት ተኩል እንደማይበልጥም ነው የተናገረችው::

ሁነቱ ለብዙዎች የማይመስል ወይም የሚከብድ እንደሆነ የተናገረችው ወጣቷ እሷ ግን ቀደም ብላ አስባበት ልምምድ ስታደርግ በመቆየቷ ወገቧን ጠበቅ አድርጋ መፈፀሟን ነው ትኩረት ሰጥታ የተነገረችው::

ወጣቷ አትላንቲክ ውቅያኖስን ስታቋርጥ ደህንነቷን የሚጠብቅ ተከላካይ አጋር ያልነበራት እና ብቻዋን መሆኑ ባለሦስት ክብረ ወሰኗ ጀግኒት ለማለት እንደሚያስደፍር ነው ያረጋገጡት- ድረገፆች::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here