አማርኛ ቋንቋ የአፍሪካ ሕብረት የሥራ
ቋንቋ እንዲሆን ተጠይቋል፤ በይፋ ጥያቄውን
ያቀረቡት የኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ናቸው። የአፍሪካ
ሕብረት መመሥረቻ ቻርተር ከተፈረመባቸው
አራት ቋንቋዎች አንዱ መሆኑንም ሚኒስትሩ
አስታውሰዋል።
ሕብረቱ ከአንድ ዓመት በፊት ስዋህሊ
ቋንቋን የሕብረቱ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን መወሰኑ
ይታወሳል::
44ኛው የአፍሪካ ሕብረት ሥራ
አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ
ተካሂዷል። የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት
ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በተሳተፉበት ስብሰባ
አምባሳደር ታዬ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፤
በዚህም የአፍሪካ ሕብረት የአማርኛ ቋንቋን
የሥራ ቋንቋው እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርበዋል።
ሚንስትሩ በንግግራቸው አክለውም
“የቀድሞው አፍሪካ አንድነት ድርጅት አማርኛ
አንደኛው የሥራ ቋንቋ እንደሚያደርግ በወቅቱ
ተነግሮ ነበር፣ ይህ እስካሁን ውሳኔ ሳያገኝ
ቆይቷል” ብለዋል።
አፍሪካ ህብረት አሁን ላይ ስዋህሊን ጨምሮ
እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ አረብኛ፣ ስፓኒሽ እና
ፖርቹጊዝ የሥራ ቋንቋው አድርጓል።
መረጃው የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ
ሚኒስቴር ነው