አሻጋሪ የሚፈልገዉ

0
48

ክልሉ በገጠመው የጸጥታ ችግር ባለፉት ሁለት ዓመታት ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎችን ከትምህርት ውጪ አድርጓል:: እነዚህ ተማሪዎች እና ሌሎችም በዚህ ዓመት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ታዳጊዎች አሁናዊ ተማጽኖ ትምህርት እንዲጀመር ነው፤ ተጀምሮ እንዳይቋረጥ:: መንታ መንገድ ላይ ቆመው የነገ ሕልማቸውን እየተመለከቱ የሚገኙት የዛሬዎቹ ታዳጊዎች፣ የነገዎቹ ሀገር ተረካቢዎች አሻጋሪ ፈልገው እጃቸውን እንደዘረጉ ናቸው:: ሚሊዮኖች በቆሙበት እንዳይቀሩ፣ ወደ ቁልቁለቱም ገብተው መውጫ እንዳያጡ ኃላፊነት ተሰምቶት እጁን የሚዘረጋው ማነው፤ የነገ መሪዎቼ የዛሬዎቹ ታናናሾቼ ናችሁ ብሎ በመስዋዕትነት የሚያሻግራቸውስ ማነው? ጥያቄው ከማንም ምላሽን አይፈልግም፤ ሁሉም ያለው በእያንዳንዱ አዕምሮ ውስጥ ነውና::

አሻጋሪ አጥተው ባሉበት ቆመው ዛሬም የክልሉን ሰላም መሆን አብዝተው ከሚጠባበቁ ታዳጊዎች መካከል ተማሪ መስከረም ውድነህ አንዷ ናት:: መስከረም በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በጨንታ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአምስተኛ ክፍል ተማሪ እያለች ነው ትምህርቷን ያቋረጠችው::

መስከረም ከትምህርት ውጪ ሆና በቆየችባቸው ጊዜያት ከብት በመጠበቅ እና እንጨት በመልቀም ቤተሰቧን ስታግዝ ቆይታለች:: ትምህርት ስትጀምር ትልቁ ህልሟ የነበረው መምህር ሆኖ ቤተሰቧ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ማስቻል ነው::

መስከረምን ያገኘናት ለመስቀል በዓል የሚሆን ችቦ እየሸጠች ነው:: ከችቦ ሽያጭ በምታገኘው ገቢ የትምህርት ቁሳቁስ የመግዛት ልምድ እንዳላት ለአሚኮ ገልጻለች፣ ይህም ዘንድሮ ትምህርት የመጀመር ከፍተኛ ፍላጎት  እንዳላት የሚያሳይ ነው::

የመርዓዊ ከተማ ነዋሪው ተማሪ አበበ ጸጋዬ በበኩሉ በ2016 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ተማሪ እንደነበር ለአሚኮ ተናግሯል:: በሰላማዊ አካባቢ የሚኖሩ ጓደኞቹ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጁ መሆኑን ሲያስብ ቁጭት እንደሚሰማው ተናግሯል::

አሁን ላይ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ተከትሎ ትምህርት መጀመሩን አስታውቋል:: በዚህም ደስተኛ መሆኑን ነው የገለጸው:: የሰላም ሁኔታው ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል ሲገልጽ የብዙዎች የትምህርት ተስፋ ዛሬም እንዳይከስም ጽኑ ምኞቱ  ነው ብሏል::

የሰሜን ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ የሺወርቅ ድረስ እንደገለጹት በክልሉ በተከሰተው የፀጥታ ችግር  በዞኑ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል:: በርካታ ተማሪዎች እና መምህራንም ከመማር ማስተማር  ውጭ ሆነው ቆይተዋል።

በ2018 የትምህርት ዘመን ወላጆች ልጆቻቸው ከትምህርት ርቀው በመክረማቸው ከፍተኛ ቁጭት አሳድሮባቸዋል:: “ዘንድሮ ትምህርት ቤቶች መዘጋት የለባቸውም“ የሚል እምነት ያላቸው ምክትል ኃላፊዋ፤  ባሁኑ ወቅት የተመዘገቡ ተማሪዎች ትምህርት መጀመራቸውን ተናግረዋል:: ምዝገባው መቀጠሉንም ጠቁመዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አከላት ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደተገለጸው ዞኑ በ2016 የትምህርት ዘመን አንድም ተማሪ ሳያስፈትን የቀረ ብቸኛው ዞን መሆኑ ተጠቁሟል:: የትምህርት መምሪያ ኃላፊው አቶ የስጋት ደሴ የ2017 የትምህርት ዘመን በአንጻራዊነት የተሻለ መነቃቃት የተፈጠረበት ሲሆን ከአንደኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል ከ37 ሺህ 180 በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ማስፈተን መቻሉን አንስተዋል።  ይሁን እንጂ በትምህርት ዘመኑ ከ359 ሺህ 360 በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አለመምጣታቸውን አመላክተዋል። ከ169 በላይ ትምህርት ቤቶች ውድመት ደርሶባቸዋል::

አሁንም በ2018 የትምህርት ዘመን ከትምህርታቸው የተፈናቀሉ ተማሪዎችን ለመመለስ በንቅናቄ እየተሠራ ይገኛል። በዚህም በ600 ትምህርት ቤቶች 426 ሺህ ተማሪዎችን ለመመዝገብ አቅዶ እየሠራ ነው:: እስካሁን ባለው ሂደት በ87 ትምህርት ቤቶች 60 ሺህ ተማሪዎች ብቻ መመዝገባቸውን ተናግረዋል። በዚህም አገላለጽ መሠረት ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ከ336 ሺህ በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አልተመለሱም:: 513 ትምህርት ቤቶችም ከተማሪ እና መምህራን ጋር አልተገናኙም።

“የትምህርት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው አንገብጋቢ ተልዕኮ ነው“ ያሉት አቶ የስጋት፤ ክልሉ  የገጠመውን ችግር ለመቀልበስ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል። በትምህርት ዘርፉ ላይ የተደቀነውን ፈተና ለመሻገር የተማሪ ወላጆች ሚና የጎላ በመሆኑ  ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኀበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በ2016 የትምህርት ዘመን ስድስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ተማሪዎችን ለማስተማር ቢታቀድም ሁለት ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አለመምጣታቸውን አስታውሰዋል።

በ2017 ዓ.ም ደግሞ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር ታቅዶ ከነበረው 4 ሚሊዮን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አልመጡም። ከተመዘገቡት ተማሪዎች መካከልም ብዙዎቹ አቋርጠው መክረማቸውን ዶክተር ሙሉነሽ ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት ከትምህርት ገበታ ርቀው የነበሩ ተማሪዎች በ2018 የትምህርት ዘመን ከትምህርት ውጪ ሆነው እንዳይከርሙ ታሳቢ ያደረገ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱን ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) አብራርተዋል::  በትምህርት ዘመኑ ሰባት ሚሊዮን 445 ሺህ 545  ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ዕቅድ መያዙንም አስታውቀዋል:: እንደ ክልል ምዝገባ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ባለው ሂደት ሦስት ሚሊዮን ተማሪዎችን መመዝገብ እንደተቻለም ገልጸዋል:: ይህም ቁጥራዊ አኃዝ የሚያሳየው የተማሪ ምዝገባው አሁንም ከፍተኛ ርብርብ እንደሚጠይቅ ነው::

በመሆኑም አሁንም በዕቅድ የተያዙት ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሄደው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ወላጆች፣ የትምህርት ማኅበረሰቡ፣ በየደረጃው ያለው የፖለቲካ አመራር፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ሌሎች ትምህርት ላይ ትኩረት አድርገው የሚሠሩ አካላት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል:: በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ ወገኖችም ትምህርትን ከፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ ውጪ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል::

መረጃ

አሻጋሪ የሚፈልገዉ

የመስከረም 19 ቀን 2018

  • በአማራ ክልል በ2016 ዓ.ም 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለማስተማር  ከታቀደው ውስጥ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን  ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አለመምጣታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
  • በተመሳሳይ በ2017 ዓ.ም ከ 7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 4 ሚሊዮን የሚሆኑ ወደ ትምህርት ቤት አልመጡም፡፡
  • በ2018 የትምህርት ዘመን 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ከታቀደው ውስጥ ከ3ሚሊያን በላይ ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡

(ስማቸው አጥናፍ)

በኲር የመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here