ሚያዚያ 9 ቀን 1857 ዓ.ም 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት አብርሀም ሊንከን በነፍሰ ገዳይ ጥይት በተመቱ በማግሥቱ አረፉ።
ፕሬዚደንት አብርሀም ሊንከን የመድረክ ትርዒት በሚያዩበት የፎርድ ቴአትር ውስጥ ነፍሰ ገዳዩ ጆን ዊልክስ ቡዝ በጥይት መታቸው። ሕይወታቸው በማግሥቱ አለፈች።
ጥቁሮች ከባርነት ነፃ እንዲወጡ ባላቸው ፅኑ እምነት በወቅቱ የነበሩት የደቡብ ባሪያ አሳዳሪዎች እርሳቸው በመመረጣቸው ደስተኞች አልነበሩም። በመሆኑም በአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት ደቡቡ በመሸነፉ የተናደደ አካል እንደገደላቸው በታሪክ ይወሳል።