አወዛጋቢዉ የምረጡኝ ቅስቃሳ ፖስተር

0
33

በኢራቅ ኪርኩክ ቀጣና በፓርላማ ምርጫ ወንበር ለማግኘት ለምትንቀሳቀሰው ሚስቱ ባል የራሱን ምስል በፓስተሮች ላይ አሳትሞ በየአደባባዩ መታየቱ ውዝግብ ማስነሳቱን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ በጥቅምት ወር መጨረሻ አስነብቧል፡፡

ድረ ገጹ እንዳስነበበው በኢራቅ የፓርላማ ምርጫ የመሐመድ አልሃልቡሲ ታቃደም ፓርቲን ወክላ ለምትወዳደረው ሻይማ ሳሚ ለመቀስቀስ በተተከሉ ትልልቅ ፖስተሮች የእጩ ተወዳዳሪዋ ምስል ሳይሆን የባለቤቷ ብቻ ነው ታትሞ ለእይታ የበቃው፡፡ ፖስተሩን ለተመለከቱትም የተወዳዳሪዋ ባለቤት ሼህ አህመድ ኢብራሂም እንደሚፎካከሩ እንጂ ተወዳዳሪዋን የሚገልፅ ምስል አለመታየቱ ግራ አጋብቷል፡፡

በርካቶችም የተወዳዳሪዋ ምስል በፖስተሮች አለታየት፣ ባለቤቷ እና የቅርብ ዘመዶችዋ በየቅስቀሳ መድረክ ተገኝተው መቀስቀሳቸው ወ.ዘ.ተ በፓርላማው የሚመርጣቸውን ህዝብ ለማገልገል ቁርጠኛ ያለመሆናቸው አብነት ነው የሚል ትችት ሰንዝረዋል፡፡

ከፊሎቹም አባወራው ባለቤቱን ወክሎ በፖስተሮች መታየቱን በመንቀፍ  ይሄ በራሱ ኋላ በተለያዩ መድረኮች ወይም በአመራር ስራዎች ውጤታማ ሆኖ መስራት ያለመቻል ማሳያ ነው በሚል ተችተዋል፡፡

የሻይማ ሳሚ ያልተለመደ የምረጡኝ የቅስቀሳ ፖስተር በማህበራዊ ሚዲያ በርካቶችን ማነጋገሩን ድረ ገጹ አስነብቧል፡፡ የሴቶች መብት ተከራካሪ ወይም ቀስቃሾች ተወዳዳሪዋ ለመመረጥ ከጀርባ ተሸሽጋ በውክልና ሳይሆን ፊት ለፊት መውጣት እንደነበረባት ነው አፅንኦት ሰጥተው ያሰመሩበት፡፡

በመጨረሻም የኢራቅ ተስፋ የተሰኘ ድርጅት መሪ ሱሩድ ሙሀመድ ዕጩ ተወዳዳሪዋ ፊት ለፊት ምስሏ አለመታየቱ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር በመጠቆም ነው ያደማደሙት፡፡:

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የህዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here