የ90 ዓመቱ አዛውንት ከዓለም አቀፉ የክብረ ወሰን መዝጋቢ ድርጅት በእድሜ አንጋፋው የጭነት መኪና አሽከርካሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን ዩፒ አይ ድረ ገጽ ለንባብ አብቅቶታል::
የ90 ዓመቱ አዛውንት ዴይሊ አርቸር ላለፉት 60 ዓመታት ከባድ መኪና በማሽከርከር ላይ ያሉ የዕድሜ ባለፀጋ መሆናቸውን አረጋግጦ ለክብረወሰን አብቅቷቸዋል- የዓለም ክብረ ወሰን መዝጋቢው ድርጅት::
ላለፉት የመጨረሻዎቹ 20 ዓመታት ከፊልፕስ በርግ “comes.inc” ለተሰኘ ድርጅት ከባድ መኪና ያሽከረከሩ መሆናቸውን አረጋግጧል- ድርጅቱ:: በአጠቃለይ ላለፉት 60 ዓመታት ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ርቀት ማሽከርከራቸውንም ነው ድረ ገፁ ለንባብ ያበቃው::
አዛውንቱ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ዴይሊ አርቸር “አሁንም በህይወት እስካለሁ ድረስ ማሽከርከሬን አላቆምም:: በእኔ አእምሮ ጡረተኛ የሚል ቃል አልተመዘገበም” ብለዋል::
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም