አዲሱ ዘላቂ አማራጭ

0
109

በቆሻሻ ማጠራቀሚያ የሚጣል ከፍተኛ መጠን ያለውን  ያገለገለ ጐማ በተለመደው ዳግም ለተመሳሳይ አገልግሎት የማዋል ሂደት ከሚያስከትለው ብክለት በፀዳ አዲስ ዘላቂ  አማራጭ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚቻል  ሳይንስ ዴይሊ ድረገጽ አስነብቧል::

በአሜሪካ የሰሜን ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ ለንባብ እንዳበቃው በአገሪቱ በ2021 እ.አ.አ ብቻ 274 ሚሊዬን ጐማ አገልግሎት ላይ ውሏል:: ከዚህ  ውስጥ አንድ አመስተኛው በቆሻሻ ሲጣል ቀሪው ዳግም ለተመሳሳይ አገልግሎት እንዲውል ተደርጓል::

የካሮላይና ዩኒቨርሲቲ ተመራማራዎች ግን በቆሻሻ ጉድጓዶች የሚጣለውን ያገለገለ ጐማ በአዲስ ስልት በዘላቂ አማራጭ አገልግሎት ላይ የማዋል የምርምር ውጤትን ነው ይፋ ያደረጉት:: በዚህም

ዶክተር አሌክሳንደር ዚክሆቪትስኪ፣ ዌልያም አርኬናን እና ሌሎች ባልደረቦቻቸው ያገለገለ ጐማን ለማጣበቂያ ሙጫ (EPOXY RESINS) ማዋል የሚያስችል አዲስ ዘላቂ አማራጭን አስተዋውቀዋል::

እስከ አሁን ሲሰራበት የነበረው በዋናነት ያገለገለ ጐማን  ለዳግም አገልግሎት በማብቃቱ ሂደት  “በፖሊመር” ስሪት ውስብስብነት የተነሳ ጥቅም ላይ ማዋል አስቸጋሪ እንደነበረም ነው የተመላከተው::

በዚሁ የኘላስቲክ የጀርባ አጥንት የሆነውን ማጠንከሪያ ይዘቱን ለማላላት የመሞከር ሂደት ዝቅተኛ እሴት ያለው ውጤትን ማስገኘቱም ነው በአሉታዊነት እጥረት ሆኖ የሰፈረው::

በመጨረሻም ዋና ተመራማሪ እና የምርምር ቡድኑ መሪ ዶ/ር ዙክሆቪትስኪ አዲሱ የምርምር ስራቸው ከዚህ በፊት የተጠቀሱትን ፈተናዎች በአሸናፊነት ለመወጣት የሚያስችል ስልት መሆኑን ነው አፅንኦት ሰጥተው ያሰመሩበት::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here