አዲዮስ እርጅና

0
139

የህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

የ59 ዓመቷ የልጅ ልጆችን ያዩ ጐልማሳ በአንድ ሰዓት 1575 “ፑሽ አኘ” በመስራት ክብረ ወሰን በመያዛቸው በዓለም የድንቃ ድነቅ መዝገብ ስማቸው መስፈሩን የዓለም አቀፍ የድንቃድንቅ መዝገብ ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት አስነብቧል::

የልጅ ልጆችን አይተው አያት የሆኑት ዶናጂን ዊልድ በአንድ ሰዓት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው “ፑሽ አኘ” የመስራታቸውን ለክብረ ወሰን በቅተዋል:: የጐልማሳዋን ክብረ ወሰን በእጅጉ የሚያልቀው ከሳምንት በፊት  “በሆድ ኘላንክ” በእግር ጥፍሮቻቸው እና ሁለት ክንዶቻቸውን ተመርኩዘው አራት ሰዓት ከ30 ደቂቃ በመቆየት ክብረ ወሰን ካገኙ ከሳምንት በኋላ መሆኑን በየድረገፆች የተሰጡ አስተያየቶች ጠቁመዋል::

ጐልማሳዋ ዶናጂን የመጀመሪያውን ክብረ ወሰን ለማስመዝገብ የሰሩት የአካል ብቃት ልምምድ ለሁለተኛው ማለትም በአንድ ሰዓት በርካታ “ፑሽ አኘ” በመስራት ክብረወሰን ለመያዝ እንዳበቃቸው ነው ያረጋገጡት::

በአሜሪካ አልበርታ ግዛት ተራሮችን በመውጣት እና በመውረድ ከቤተሰባቸው አባላት ጋር ልምምድ ማድረጋቸው አእምሯዊም ሆነ አካላዊ ዝግጁነት እንደፈጠረላቸው ነው የጠቆሙት – ጐልማሳዋ::

በጡረታ ከመገለላቸው በፊት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ርእሰ መምህር ሆነው ያገለገሉት ጐልማሳዋ ተሰማርተውበት የነበረው ሙያም የመንፈስ ጥንካሬን እንዲሰንቁ ያስቻላቸው መሆኑን ነው የገለጹት:: ሁለተኛውን ክብረወሰን ሲያዝመዘግቡ ከ12 የልጅ ልጆቻቸው በ11ዱ ተከበው እያንዳንዷን “ፑሽአኘ” ሲቆጥሩ የሚያሰሙት ድምፅ አብርትቷቸው ካሰቡት ጣሪያ ማለፋቸውን ነው በኩራት የተናገሩት:: ዶናጂን ሁለተኛውን ክብረወሰን ካስመዘገቡ በኋላ ከደጋፊዎች እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ፎቶግራፎችን ተነስተዋል::

በማጠቃለያነት ለጤናማነት ግቦችን አስቀምጦ ከተጉ በፀጋ እና በጥንካሬ የእርጅና ዘመንን እያሸሹ መቆዬት እንደሚቻል ነው ያረጋገጡት::፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here