አዳኝ ለአዳኝ

0
174

ለመጀመሪያ ጊዜ በተመዘገበ የዝርያዎች መስተጋብር ወደ ባሕር ጠለል ቀርቦ ሲያስስ የነበረን ባለነጭ ጭራ ንስር ለመከላከልና ለማባረር የባህር አንበሳው ሽቅብ የውሀ ጅረት ሲያስወነጭፍ በምስል  ሊቀረጽ መቻሉን ዩፒአይ ድረ ገጽ  አስነብቧል፡፡

በእንግሊዝ የዋይት ደሴትን በከበባት ባህር ግራጫ መልክ ያለው የባሕር አንበሳው  ወደ ባህሩ የላይኛው ክፍል ዝቅ ብሎ የሚያንዣብበውን ባለ ነጭ ጭራ ንስር ለመከካለከል እና ለማባረር ሽቅብ የውሀ ጅረት ሲያስወነጭፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በምስል መቅረጽ ተችሏል፡፡

የተቀረፁትን ምስልም አንሺዋ ክሌር ጃኮብስ ለፓርትስማውዝ ዩኒቨርሲቲ አስረክበዋል፡፡ የፓርትስማውዝ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችም ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳውን የሁለቱን ዝርያዎች መስተጋብር የሚያሳየውን ምስል ለበለጠ ሰፊ ጥናት መነሻ ማድረጋቸው ነው የተገለፀው፡፡

ንስሩ ወደ ባሕሩ የላይኛው ክፍል ተጠግቶ በማሰስ ላይ ሳለ ከባህሩ ውስጥ ከፍ ያለ የማስጠንቀቂያ ጩኸት ከባህር ዓሳው መሠማቱን አስረድታለች፡፡ ሁነቱን የቀረፀችው ክሌር ጃኮብስ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የጂኦግራፊ እና ጂኦ ሳይንስ ትምህርት ክፍል የቅሪት አካላት ተመራማሪ የሆኑት ሜጋን ጃኮብስ እናቷ ባነሱት የመጀመሪያ በሆነው የዝርያዎች መስተጋብር ማሳያ ፎቶ ግራፍ መነሻነት አዲስ ጥናታዊ ጽሁፍ መሥራታቸው ነው የተገለፀው፡፡

ሁለቱ ዝርያዎች ዋይት ደሴትን በከበባት ዳርቻ ቀደም ባሉት ዓመታትም መታየታቸው ቢታወቅም የባሕር አንበሳው ዓሳ ለማደን የሚያንዣብበውን ንስር ለማባረር ውሀን እንደ መከላከያ ማስወንጨፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተቀርፆ ለእይታ የበቃው፡፡

የተቀረፀው ምስል በቀጣይ የመስኩ ምሁራን ለሚያደርጉት ሰፊ ጥናትና ምርምር የመሠረተ ድንጋይ እንደሚሆን ነው በአጽንኦት ያስታወቁት – ተመራማሪዎቹ፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here