አጭሩ ብሔራዊ ድንበር

0
179

ፔኖን ዲ ቪሌዝ ጎሜራ በ1564 እ.አ.አ በስፔን ቅኝ ግዛት ስር የወደቀች 85 ሜትር ብሔራዊ ድንበር ያላት ሃገር መሆኗን ኦዲቲ ሴንትራል ድረገጽ አስነብቧል።

ስፔን 2000 ኪሎሜትር ከፖርቹጋል እና ፈረንሳይ ጋር አጭር ድንበሮች አሏት።

ስፔን በዓለማችን አጭር ድንበር ከአፍሪካዊቷ ሞሮኮ ጋር ትጋራለች። በዚህም 85 ሜትር ልኬታ ድንበር፤ 19 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት ያለው ንጣፍ አለት አላት። ይህም የሚያዋስነው ድንበር አጭሩ የዓለማችን ድንበር ሆኖ ተመዝግቧል።

ፔኖን ዲቬሌዝ ዴላ ጎሜራ በስፔን ቁጥጥር ስር የዋለችው በአድሚራል ፔኖን ደስቶፒና ፊታውራሪነት በተደረገ ዘመቻ ነበር። ሞሮኮ በተደጋጋሚ የግዛቲቱን የይገባኛል ጥያቄ ብታቀርብም ተቀባይነት ባለማግኘቷ በስፔን ቁጥጥር ስር ቀርታለች። ስፔንም ግዛቲቱን ለማስከበር ወታደሮችን አስፍራበታለች። ወታደቹም ግዛቲቱን ለመከላከል ብቻ ነው የሰፈሩት። ለዚህም ወታደሮቹ በየተራ ይፈራረቃሉ።

ግዛቲቱ ምንም ዓይነት ተቋማት የሏትም። ኤሌክትሪክ እና መሠል አገልግሎትም እንዲሁ። ለወታደሮቹ የተለያዩ አቅርቦቶች የሚቀርቡላቸው በስፔን ባህር ሃይል ነው።

በ2012 እ.አ.አ. ሰባት ወታደሮች ሰርገው ወደ ግዛቲቱ በመግባት  ጥቃት ቢፈጽሙም በስፔን ወታደሮች ተሸንፈው አሁንም በስፔን ቁጥጥር ስር ቀርታለች።

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here