ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ የኢትዮጵያን የፖስታ አገልግሎት ለማቋቋም በማሰባቸው የዓለም ፖስታ ማህበር አባል ለመሆን ለስዊዝ ፕሬዚደንት በድጋሜ ደብዳቤ የላኩት በያዝነው ሳምንት መጋቢት 10 ቀን 1887 ዓ.ም ነበር።
ንጉሡ ከዚህ በፊት የካቲት 10 ቀን 1885 ዓ.ም ላይ በላኩት ደብዳቤ የጠየቁ ቢሆንም የተሰጣቸው ምላሽ በቅድሚያ የፖስታ ስራ ማካሄዱን እንዲጀምሩ የሚል ነበር። በመሆኑም በ1886 ዓ.ም በፓሪስ ውስጥ በምስላቸው የተቀረፀ ቴምብር በስራ ላይ አዋሉ። ይህን ካደረጉ በኋላ ነበር በድጋሜ የፃፉት፣ ከዛሬ 129 አመታት በፊት በፊት መሆኑ ነው።
ምንጭ፤ ጳውሎስ ኞኞ
(መሰረት ቸኮል)
በኲር መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም