ኤቨረስትን የረታችው

0
45

ቤላሩሲያዊቷ አልጋ ናውሞቫ ወደ ኤቨርስት ተራራ በሄሊኮፐተር ከወጣችበት 6384 ሜትር ከፍታ በፓራሹት ተንሳፋ ግግር በረዶ ከረገጠችበት 3766 ሜትር እግሯ ላይ በተሰራው መንሸራተቻ ጣውላ 2438 ሜትር ድረስ በመውረድ ጀብደኛነቷን ማስመስከሯን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡

አልጋ ናውሞቫ ያከናዎናቸው በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረ “ስካይ ሰርፊንግ” የተሰኘ ትርኢት ሲሆን ከአውሮፕላን በዣንጥላ ወርዶ በረዶ ላይ ማረፍ ከዚያም እግር ላይ በታሰረው መንሸራተቻ ቁልቁል መውረድን ያጠቃለለ ነው፡፡

ስፖርተኛዋ አልጋ ባለፈው የህዳር ወር መጀመሪያ በኒማሊያ ተራራ ኤቨረስት ግግር በረዶ ላይ ለማረፍ ኃይለኛውን የነፋስ ግፊት መቆጣጠር እና ወደምትፈልገው አቅጣጫ ለማምራት በእጅጉ እንደተፈተነች አስነብቧል- ድረ ገጹ፡፡

ሆኖም ጠንካራዋ አልጋ ባደረገችው ብርቱ ጥረት ከነፋሱ ግፊት አቅጣጫ የዣንጥላውን አቅጣጫ ወጥራ 3766 ሜትር ከፍታ ካለው አልፎ አልፎ ዛፎች ከሚታዩበት ግግር በረዶ አቀበት ላይ በእግሯ ማረፍ  ችላለች፡፡

ቀጥላም እግሯ ላይ የታሰረውን የመንሸራተቻ ጣውላ ወይም “ስኬት ቦርድ” በመጠቀም ሚዛኗን ጠብቃ  እየተጠማዘዘች የጉዞ አቅጣጫዋን በማስተካከል በቁልቁለት ግስጋሴዋ ገፍታ በተወሰኑ ደቂቃዎች ውስጥ 2438 ሜትር መድረሷን ድረ ገፆች አስነብበዋል፡፡

ቤላሩሲያዊቷ አልጋ ናውሞቫ ድፍረትን እና ፅናትን በሚሻው የስፖርት ዓይነት ተፈትና ጉልበቷ ሳይዝል ያሰበችውን በማሳካቷ መደሰቷንም ድረ ገጹ በማጠቃለያነት አመላክቷል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጥር 11  ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here