እንደየ ፈላጊዎች የዘመኑ

0
164
ፍላጐትን መሠረት አድርገው፤ የጥራት መስፈርቶችን ያሟሉ፣ ከዋጋ ተመጣጣኝነት እስከ ከፍተኛ የአፈፃፀም አቅም ያላቸው ላኘቶፖች በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት ለተጠቃሚዎች መቅረባቸውን ቴክኖሎጂ ዶት ኦርግ ለንባብ አብቅቶታል::
በ2024 እ.አ.አ ተመርተው ገበያ ላይ የዋሉት ዘመናዊዎቹ ላፕቶፖች በወጪ ተመጣጣኝ ናቸው:: ለዘርፈ ብዙ አገልግሎት ምቹነትን መሠረት አድርገዋል:: ደረጃቸውም፦
አንደኛ፡- አሰር አስፓዬር አምስት – በቀዳሚነት ተቀምጧል:: ጥንካሬን ከዋጋ ተመጣጣኝነት ጋር ያጣመረ ነው:: ስምንት ጂቢ ራም ሚሞሪ አለው:: ክብደቱ ደግሞ ሦስት ነጥብ 75 ፓውንድ ተለክቷል:: ለተጠቃሚዎች ከተመቸ ስክሪን እና የቁልፎች ሰሌዳ ጋር የተደራጀ ነው::
ሁለተኛ፡- አኘል ማክቡክ ኤይር ኤም ሁለት – በተማሪዎች የሚመረጥ፤ የባትሪው ኃይልም 14 ሰዓት መቆየት የሚችል ነው:: ተንቀሣቃሽ የኃይል መያዥ ቋትም አለው:: የኮምፒውተሩ ማሣያ ሰሌዳ 13 ነጥብ ስድስት ኢንች ይሰፋል:: ላኘቶፑ ባለ አራት ድምፅ ማጉያ እና ከቦታ ቦታ ለማጓጓዝም ምቹነት ያለው ነው::
ሶስተኛ፡- አሰር ክሮም ቡክ ስፒን 714 ፡-የፊት ለፊት ሰሌዳው ወደ ኋላ የሚንጋለል ለተጠቃሚ ምቹነትን የሚለግስ ነው::
ፈጣን የቅንብር አሰራርን ያሰፈነ፣ በተጨማሪ ማሳያ ሰሌዳው መጠነ ሰፊ፣ እንደ ታብሌት ሁለገብነትን የሚፈቅድ ነው::
አራተኛ፦ ዴል ኤልይን ዌር ኤም17 አር አምስት- የተለያዩ ጨዋታዎችን ለሚያዘወትሩ ተመራጭ ነው::በቀላል ንድፍ ከፍ ያለ የኃይል አፈፃፀምን ተጭኗል:: ላኘቶፑ ለዘርፈ ብዙ አገልግሎትም ተመራጭ ነው::
አምስተኛ፡- ዴል ኤክስፒ ኤስ 15 – በ2024 ለዘረፈ ብዙ ተግባራት ይመረጣል-ይወደሳልም::
ስክሪኑ ሰፊ ነው:: ውበትን ከአፈፃፀም ጥራት ጋር አጣምሯል::
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here