ከባቢ ዓየርን መራዡ

0
189

የሰደድ እሳት በእጽዋት እና በአፈር ውስጥ የሚገኝ
የብረት ንጥረ ነገርን በሙቀት ወደ መርዛማ ትነትነት
ለውጦ ወደ ከባቢ ዓየር በመቀላቀል የከፋ ጉዳት
እንደሚያደርስ ቴክኖሎጂ ዶት ኦርግ ባለፈው ሳምንት
ለንባብ አብቅቶታል፡:
በአሜሪካ የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች
ባካሄዱት አዲስ ጥናት እንዳረጋገጡት የሰደድ እሳት
በእጽዋት እና በአፈር ውስጥ የሚገኝ “ክሮሚያም 3”
የተሰኘ ንጥረ ነገርን በሙቀት ወደ “ክሮሚየም 6” ከባድ
ብረት በመለወጥ ወደ ከባቢ አየር ተቀላቅሎ ለካንሰር
ህመም ያጋልጣል:: በዩኒቨርሲቲው የዘላቂ ልማት
ትምህርት ክፍል ተማራማሪዎቹ ዶክተር አሌክሳንደር
ሎፔዝ እና ፕሮፌሰር ስኮት ፌንደርፍር እንዳሰፈሩት
በሰደድ እሳት የሚፈጠረው ጢስ የሚያደርሰው የጤና
እክል ብቻ ነበር በውል የሚታወቀው፤ ሁነቱ ተቃሎም
ነበር የሚታየው::
በእጽዋት እና በአፈር ውስጥ የሚገኝ “ክሮሚዬም
3” ለሰዎች አካል ግሉኮስን ለመፍጨት ያገለግላል::
ከጠቃሚነቱ አልፎ የከፋ የጤና እክል የሚያስከትለው
በሙቀት ወደ “ክሮሚዬም 6” ነት ተቀይሮ ከባቢ ዓየርን
መርዛማው ትነት ሲቀላቀል መሆኑን ነው ያሰመሩበት::
የሰደድ እሳት በእጽዋት እና በአፈር ውስጥ
የሚገኝ ንጥረ ነገርን በከፍተኛ ሙቀት ወደ መርዛማ
ትነትነት በመቀየር የከፋ የጤና እክል እንደሚፈጠር
በአውስትራሊያ የደቡብ ግዛት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች
በ2019 እ.አ.አ ናሙናዎችን ሰብስበው በቤተ ሙከራ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here