ከወጪ ንግድ ምርቶች ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

0
269

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ክትትል ከሚያደርግባቸው የወጪ ንግድ ምርቶች 617 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በስምንት ወሩ ከዘርፉ ወጪ ንግድ 705 ነጥብ 15 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ የእቅዱን 87 ነጥብ 51 በመቶ አፈፃፀም ተመዝግቧል፡፡

ገቢው ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት አፈፃጸም ጋር ሲነፃጸር የ80 ነጥብ 08 ሚሊዮን ዶላር ወይም 14 ነጥብ 91 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል፡፡

ሚኒስቴሩ በማሕበራዊ ትሥሥር ገጹ እንዳስነበበው የጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች ከፍተኛውን ገቢ ያስገኙ ምርቶች ናቸው፤ የውልና ኢንቨስትመንት እርሻ መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ደግሞ ለተመዘገበው ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም የአኩሪ አተር፣ ቀይ ቦሎቄና ማሾ ምርቶች የዓለም አቀፍ ገበያ ፍላጎት መሻሻሉ እንዲሁም የሰሊጥ ምርት መጨመር በዘርፉ ለተገኘው ውጤት ማደግ ተጠቃሽ ምክንያቶች እንደሆኑ ተመልክቷል።

(ሳባ ሙሉጌታ)

በኲር ሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here