ከ157 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆኑ

0
191

በአማራ ክልል ከሐምሌ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ምክንያት ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለዋል። በትምህርት ዘርፉ ላይ በፈጠረው ጫና በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል::

በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ውስጥም 157 ሺህ 785 ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አለመመለሳቸውን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ገልጿል። 382 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶችም የመማር ማስተማር ሥራ ማቆማቸው ተነግሯል።

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ትግበራ ቡድን መሪ አጥናፍ መከተ ክስተቱ የሕጻናትን የነገ ተስፋ የሚያጨልም እና በሀገር ላይ ተሻጋሪ ችግሮችን የሚያስከትል በመሆኑ የትምህርት ተቋማት የቀውሱ ሰለባ መሆን እንደሌለባቸው አስገንዝበዋል።

መንግሥት እና ሕዝብ እያደረጉ ባሉት የሰላም ጥረት የፀጥታ ሁኔታው መሻሻል በታየባቸው ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የመማር ማስተማር ሥራን ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ቡድን መሪው ተናግረዋል::

(ሳሙኤል አማረ)

በኲር መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here