ከ39 ሺህ ሄክታር በላይ ሰብል ተሰብስቧል

0
128

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን በ2016/2017 የምርት ዘመን 286 ሺህ 211 ሔክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።
የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ አለኸኝ ለበኩር በስልክ እንደተናገሩት፤ በምርት ዘመኑ 271 ሺህ 411 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 286 ሺህ 211 ሔክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል። በዞኑ ጤፍ፣ በቆሎ እና ገብስ በስፋት እንደሚመረትም ነው የተናገሩት።
አቶ መልካሙ እንዳሉት በዘር ከተሸፈነው መሬት ውስጥ መረጃው እስከተጠናቀረበት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 39 ሺህ 216 ሄክታር ሰብል ተሰብስቧል። በዘር ከተሸፈነው የሰብል ማሳ ውስጥ ገብስ፣ ቦሎቄ፣ አተር እና ባቄላ ሙሉ በሙሉ እንደተሰበሰበ ተናግረዋል። በሰብል ስብሰባውም 62 ሺህ 432 አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል። በቆሎ፣ አኩሪ አተር እና ሰሊጥ በጥቅምት ወር መጨረሻ ሳምንት የመሰብሰብ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
በዞኑ በሁሉም አካባቢ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እየዘነበ በመሆኑ አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት እና በወቅቱ በመሰብሰብ የምርት ብክነትን መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል።
አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎችን በደቦ መሰብሰብ፣ ከፍ ባለ ቦታ መከመር፣ ዝናብ የሚከላከሉ ኘላስቲኮችን ክምሩን ማልበስ እና ቶሎ ወቅቶ ወደ ቤት ማስገባት ያስፈልጋል ብለዋል።
በአጠቃላይ በዞኑ በምርት ዘመኑ 13 ሚሊዮን 160 ሺህ 85 ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

(መልካሙ ከፋለ)

በኲር የጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ዓ.ም ዕትም)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here