ክብረ ወሰናቸውን ያስመለሱት

0
166

አሜሪካዊው አልፍሬድ ብሌሽክ በመቶ ስድስት ዓመት ዕድሜያቸው ከረዳታቸው ጋር ተጣምረው በዘጠኝ ሺህ ጫማ ከፍታ ሲበር ከነበረ አውሮኘላን በመዝለል ዳግም ለክብረወሰን መብቃታቸውን ዩፕአይ ድረገጽ  ለንባብ አብቅቶታል::

በ2020 እ.አ.አ አልፍሬድ ብሌሽክ በ103 ዓመታት ዕድሜያቸው ከአውሮኘላን በመዝለል በዕድሜ አንጋፋ ዘላይን ክብረ ወሰን ይዘው ነበር:: ሆኖም ከሦስት ዓመታት በኋላ በ2022 እ.አ.አ ሲዊዲናዊቷ ሩት ሊንኒያ ኢንግጋርድ ላርሰን የተባለች ሴት በ103 ዓመት ከ259 ቀናት በሆነው ዕድሜዋ ከአውሮፕላን ተወርወራ በመዝለሏ ክብረወሰናቸውን ለመንጠቅ ችላለች::

አልፍሬድ ብሌሽክ ዳግም የተነጠቁትን ክብረ ወሰን ለማስመለስ  የቴክሳስ ገዢ ከሆኑት ግሬግ አቦት ከተባሉ ሰው ጋር ተጣምረው ለመዝለል ስምምነት ላይ ደረሱ::  ይህንኑ ተከትሎ ህዳር 27 ቀን 2023 እ.አ.አ በዘጠኝ ሺህ  ጫማ ከፍታ ላይ ከሚበር አውሮኘላን ከአጋራቸው ጋር ተጣምረው ተወረወሩ::

አልፍሬድ ብሌሽክ በአጋራቸው እየተመሩ 5500 ጫማ ላይ ሲደርሱ “ፓራሹት” ወይም ዣንጥላቸውን መዘርጋት ቻሉ:: በዚሁም የተነጠቁትን ክብረ ወሰን አሻሽለው ለማስመለስ ችለዋል::

አዛውንቱ ሲጠባበቋቸው ለነበሩ ተመልካቾች እና ጋዜጠኞች “የማትችል ከመሰለህ ራስህን ዝቅ አድርገህ ተመልክተኸዋል ማለት ነው:: እያንዳንዱ  ሰው ከሚያስበው በላይ አቅም አለው:: ዋናው ነገር ለመሞከር መወሰን ብቻ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

 (ታምራት ሲሳይ)

በኲር ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here