ዘብ አንቂዎቹ ዝይዎች

0
188

በብራዚል ሳንታካንታሪና ግዛት የሚገኝ
ማረሚያ ቤት ለጥበቃ የሚያገለግሉ ውሾቹን
ያልተለመደ ድምጽ ሲሰሙ በከፍተኛ ጩኸት
ጥበቃዎችን በሚያነቁ የዝይ መንጋ መተካቱን ኦዳቲ
ሴንትራል አስነብቧል:: ድረ ገጹ እንዳስነበበው
በብራዚል ማረሚያ ቤት ባለፉት ዓመታት
ለታራሚዎች ጥበቃ ከአጥር ውጪ ሲያሰማራቸው
የነበሩ አነፍናፊ ውሾችን በዝይዎች ተክቷል:: የዝይ
መንጋዎች የታራሚዎችን መኖሪያ በሚከልለው
ግምብ እና የማረሚያ ቤቱ የመጨረሻ አጥር
መካከል እንዲለቀቁ ተደርጓል::
ዝይዎች ከፍተኛ ድምጽ የመስማት አቅም
ብቻ ሳይሆን ድምጹን እንደሰሙ ከፍተኛ ድምጽ
የማሰማት ብቃት እንዳላቸው በማረጋገጣቸው ነው
የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ይህንኑ ስልት ተግባራዊ
ያደረጉት:: በተጨማሪም ዝይዎችን ማግኘት እና
መቀለብ ቀላል መሆኑ ለተፈላጊነታቸው አባሪ
ምክንያት ሆኖ ተጠቅሷል::
ቀደም ባሉት ዓመታት ማረሚያ ቤቱ
ከኤሌክትሮኒክስ የጥበቃ ቁሶች እና ስልቶች ባሻገር
የሰለጠኑ አነፍናፊ ውሾችን ነበር የሚያሰማራው::
አነፍናፊ ውሾችን ለማሰልጠንም ሆነ ለመመገብ
የሚወስደው ጊዜም ሆነ የሚያስፈልገው ወጪ
ከፍተኛ መሆኑም ተጠቁሟል::
በመሆኑም ማረሚያ ቤቱ ግራ ቀኙን
አገናዝቦ ዝይዎችን ለመመገብ የሚወጣው ወጪ
አነስተኛ መሆኑ እንዲሁም ለስልጠና ብዙ ወጪ
ስለማያስፈልጋቸው ለጥበቃው በአጋዥነት
መመረጣቸውን ነው ድረ ገፁ ያስነበበው::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here