በአፈ/ከሳሽ ዘመን ኢትዮጵያ አስመጭና ላኪ እና በአፈ/ተከሳሽ 1ኛ. አቶ ታደሰ ስመኝ እንዲሁም 2ኛ. ወ/ሮ ሀብታም ወንድምአገኝ ጀንበሬ መካከል ስላለው አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በዱርቤቴ ከተማ ቀበሌ 02 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ማንደፍሮ ይዞታ፣ በደቡብ መንገድ መካከል ተዋስኖ የሚገኘውን 2800 ካ/ሜትር ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋ 12,956,134.46 (አስራ ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አምሳ ስድስት ሽህ አንድ መቶ ሰላሳ አራት ብር ከ46 ሳንቲም) ሕዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ጨረታው በሚካሄድበት በዱርቤቴ ከተማ ቀበሌ 02 ወይም ንብረቱ በሚገኝበት በመገኘት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በሰዓቱና በቦታው በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በዕለቱ ጨረታውን ያሸነፈ ያሸነፈበትን 1/4ኛውን በሞ/85 ጨረታው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ የሚያስይዝ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
የባ/ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት