የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
106

በአፈ/ከሳሽ ዘመን ኢትዮጵያ አስመጭና ላኪ እና በአፈ/ተከሳሽ 1ኛ አቶ ታደሰ ስመኝና 2ኛ ሀብታም ወንድምአገኝ ጀንበሬ መካከል ስላለው አፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በዱርቤቴ ከተማ ቀበሌ 02 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን የማንደፍሮ ይዞታ እንዲሁም በደቡብ መንገድ መካከል ተዋስኖ የሚገኘውን 2800 ካ.ሜትር ለሞቴል አገልግሎት የሚውል ከቡለኬት የተሰራ አራት ክፍል የንግድ ቤት እና ለነዳጅ ማጠራቀሚያ የሚውል መሬት ውስጥ የተቀበሩ እያንዳንዳቸው 50,000 (አምሳ ሽህ) ሊትር ነዳጅ የሚይዙ 4 ታንከሮችን ከማስተላለፊያ ቱቦዎች ጋር በመነሻ ዋጋው 12,956,134.46 (አስራ ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አምሳ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ አራት ብር ከ46 ሳንቲም) በሆነው ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ጨረታው በሚካሄድበት በዱርቤቴ ከተማ ቀበሌ 01 ወይም ንብረቱ በሚገኝበት በመገኘት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በሰዓቱና በቦታው በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣ በዕለቱ ጨረታውን ያሸነፈ ያሸነፈበትን 1/4 ኛውን በሞ/85 ጨረታው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ የሚያዝ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here