የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
77

በአፈ/ከሳሽ ግርማ ሁነኛው እና በአፈ/ተከሳሽ ጋሻው ምኒችል መካከል ስላለው አፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በባ/ዳር ከተማ ዳግ/ምኒ/ክ/ከተማ ውስጥ በአቶ አባተ እንዳለው እና በወ/ሮ ጥሩወርቅ ወርቁ ስም በይዞታ ካርታ ሴሪ ቁጥር 000590 የምዝገባ ቁጥር 04/001/1606 የቁራሽ ልዩ መለያ ኮድ AM0010508/2015 ተመዝግቦ የሚገኘውን በአዋሳኝ በምሥራቅ ፣ በሰሜን  እና በደቡብ መኖሪያ ቤት እንዲሁም በምዕራብ መንገድ ተዋስኖ  የሚገኘውን 250 ካ-ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር  1,652,127.18 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ብር ከ18 ሳንቲም) ይሸጣል፡፡  በመሆኑም ሚያዚያ 04 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ የፍ/ቤቱ ሃራጅ ባይም ጨረታው በሚካሄድበት በዳግማዊ ምኒሊክ ክ/ከተማ ንብረቱ በሚገኝበት በመገኘት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በሰዓቱና በቦታው በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን በዕለቱ ጨረታውን ያሸነፈ ያሸነፈበትን 1/4 ኛውን በሞ/85 ጨረታው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ የሚያዝ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛው ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here