የሂሳብ ምርመራ (የኦዲት) አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

0
68

የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በIFRS መሰረት ለማስመርመር በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የድርጅቱን ሂሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ፡፡
  3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸዉንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸዉ በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ፣ ከዋናዉ ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሣብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ካደረጋቸዉ የልማት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
  4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባ/ዳር ዋና መ/ቤት፣ በባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት፣ በደሴ ቅ/ጽ/ቤት እና በጎንደር ቅ/ጽ/ቤት በየከተሞች በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቀው የሚሳተፉ ፡፡
  5. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ወይም በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 (ሃያ አንድ) የስራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለዉ ከአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋ/መ/ቤት ቀበሌ 03 ባ/ዳር ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304 በመግዛት መጫረት ይቻላል ፡፡
  6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ ፣ የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ዉስጥ በባ/ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ድርጅቱ በተከራየዉ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ ፡፡  ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል::
  7. የጨረታ ሳጥኑ በ22ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ወይም እለቱ የእረፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለዉ ቀን ከቀኑ በ4፡45 በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 201 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ጨረታዉ ይከፈታል ፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅቱ ድረስ በአካል በመምጣት  አስፈላጊዉን መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት

ባህር ዳር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here