የአብክመ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ የ2016 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- የድርጅቱን ሂሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፤ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውው፡፡
- የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ፡፡
- ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዪጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፤ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ከአደረጋቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባሕር ዳር እና ኮንቦልቻ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ፣ ወይም በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 የሥራ ቀናት በኢንተርፕራይዛችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400.00 /አራት መቶ ብር/ ከፍሎ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት “የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ”፣ “የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/” 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ማስያዣን በሁለት የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የሥራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 33 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ21 ኛው ቀን፣ ከቀኑ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ወይም እለቱ የእርፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ከረፋዱ በ4፡30 በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 33 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማሳሰቢያ፡-ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 320 61 31 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ
ባህር ዳር