አፈ/ከሳሽ ኢብራሂም ጡባ እና የአፈ/ተከሳሽ መንገሻ ሹምየ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በደብረ ታቦር ከተማ ቀበሌ 01 የሚገኝ በካርታ ቁጥር 134/54/04/2000 የተመዘገበ በአወሳኝ በምሥራቅ ውባንተ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ዋና መንገድ እና በደቡብ እንዳወቅ፣ የሚያዋስነው ስፋቱ 125 ካ.ሜትር የሆነ ቤትና ቦታ በጨረታ እንዲሸጥ በመነሻ ዋጋው 9,442,357.00 /ዘጠኝ ሚሊየን አራት መቶ አርባ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ ሰባት ብር/ መነሻ በማድረግ እንድትጫረቱ ጨረታው ከመጋቢት 30/2016 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ለአንድ ወር በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ጨረታው ሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ድረስ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ይከናወናል:: በዚህ ጨረታ መሳተፍ ማንኛውም ግለስብ የጨረታውን ¼ ኛውን ወዲያውኑ በማስያዝ መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል::