በአፈ/ከሳሽ አቶ ማኔ በቀለ እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ አብዱ ዑስማን መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በባሕር ዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ በአፈ/ተከሳሽ አብዱ ዑስማን ስም የተመዘገበ በምሥራቅ እሱባለው ጌታነህ፣ በምዕራብ ዘአምላኩ ዜና፣ በሰሜን መንገድ እና በደቡብ የአለማየሁ ደግፍ መኖሪ ቤት በካርታ ቁጥር 30497 የሆነ 250 ካ.ሜ ቤት በመነሻ ዋጋ 1,364,697 /አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሰባት ብር/ ሆኖ ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ መጫረት የምትፈልጉ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በሰዓቱና በቦታው በመገኝት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የመጨረሻ አሸናፊው ያሸነፈበትን ¼ ኛውን ወዲያውኑ በሞ/85 ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ ያሳውቃል፡፡