በአፈ/ከሳሽ ዘንገና የዕቁብ ማህበር ሰብሳቢ ሻለቃ አስቻለው ይሁን አፈ/ተከሳሾች እነ አቶ ደረጄ አድማስ መካከል ባለው የብድር ገንዘብ ክርክር ጉዳይ እንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ክፍት ቦታ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን አለነ ደሜ፣ በደቡብ አስማረች ከበደ የሚያዋስነው በወ/ሮ ሙሉቀን ዘውዴ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖሪያ ቤት የሆነው መነሻ ዋጋ 2,350,000.00 /ሁለት ሚሊየን ሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ/ ስለሚሸጥ መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች ከታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ተለጥፎ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከ3:00 እስከ 6፡00 ድረስ ቦታው በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት