የአፈ/ከሳሽ ህፃን ቤዛዊት ካሳሁን ሞግዚት ህንፃ ውበት የአፈ/ተከሳሽ አዲስአለም አዘነ ጣ/ገብ ህፃን ረካን ካሳሁን መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክርክር ክስ ጉዳይ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 በአዋሳኝ በምሥራቅ ጥላሁን፣ በምዕራብ ገበየሁ፣ በሰሜን ደረጀ እና በደቡብ መንገድ ስፋቱ 200 ካ/ሜትር ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋ ብር 3,882,270.90 (ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማኒያ ሁለት ሽህ ሁለት መቶ ሰባ ከዘጠና ሳንቲም) የሆነውን የሟች ካሳሁን ጌቴና የአዲስአለም አዘነ ቤትና ቦታ ስለሚሸጥ ጨረታው የሚካሄደው ጥር 10/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ጨረታው ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 ወዲያውኑ ለመ/ቤቱ ሀራጅ ባይ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ የጨረታ ውጤቱን ያሸነፈውን 1/4 የመ/ቤቱ ሀራጅ ባይ በመያዝ ውጤቱን ለቀጠሮው ቀን ለጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲገጽ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት