የሃራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
91

በአፈ/ከሳሽ አሳዬ ጀንበር እና በአፈ/ተከሳሽ ጌትነት መንግስት መካከል ባለው ገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ በምሥራቅ ክፍት ቦታ፣ በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን አስራት ባይነስ እንዲሁም በደቡብ ክፍት ቦታ የሚያዋስነው በአቶ ጌትነት መንግስት ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖሪያ ቤት የሆነው በመነሻ ዋጋ 2,750,000 /ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ ስለሚሸጥ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከታህሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ ወጥቶ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከ3:00 እስከ 6፡00 ጨረታው የሚካሄድ መሆኑን አውቃችሁ ቦታው ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛውን ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here